ፋል ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ከአገልግሎት ተመላሽ የተደረጉ የተለያዩ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

FAL-GENERAL-CONTRACTOR-reportertenders

Overview

  • Category : Other Sale
  • Posted Date : 04/17/2022
  • Phone Number : 0116626357
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 04/22/2022

Description

 ፋል ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ

ያገለገሉ ንብረቶች ሸያጭ የጨረታ ማስታወቂያ

      ፋል ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ከአገልግሎት ተመላሽ የተደረጉ የተለያዩ ዕቃዎች፡-

  1. በአዲስ አበባ ልዩ ስሙ ቦሌ ቡልቡላ ፕሮጀክት እና አያት መቄዶንያ 49 ማዞሪያ አጠገብ በሚገኘው የቦሌ አያት ፕሮጀክት ውስጥ የሚገኙ ዝርዝራቸው በመጫረቻ ሰነድ ላይ የተዘረዘሩት  ንብረቶችን፤
  2. በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደብረ ማርቆስ ደብረ ኤልያስ ልዩ ስሙ ተምጫ ተብሎ በሚጠራው  የድርጅቱ የመንገድ ስራ ፕሮጀክት ካምፕ ውስጥ የሚገኙትን  ክፍት የሬንጅ በርሜሎች ከነክዳናቸው እና  የዘይት በርሜሎች  እንዲሁም፡-
  3. በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሐረር ባቢሌ ፊቅ ተብሎ በሚጠራው የድርጅቱ መንገድ ስራ ፕሮጀክት ካምፕ ውስጥ የሚገኙትን ክፍት የሬንጅ በርሜሎች ፤ እና የዘይት በርሜሎች  በጨረታ   አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

የተዘጋጅውን የጨረታ ሠነድ ከዚህ በታች በተመለከተ የድርጅቱ አድራሻ በመቅረብ ብር 200፡00 (ሁለት መቶ) በመክፈል  መውሰድና መጫረት ይችላሉ፡፡

የጨረታው መወዳደሪያ ሰነድን የገዙ ተጫራቾች ፤ዕቃው በሚገኝበት በአዲስ አበባ ቦሌ ቡልቡላ እና ቦሌ አያት ፕሮጀክት እንዲሁም በአማራ ክልል ደብረ ማርቆስ ደብረ ኤልያስ ተምጫ ተብሎ  በሚጠራው የድርጅቱ ፕሮጀክት ካምፕ  ውስጥ እና በባቢሌ ፊቅ (ሐረር) ፕሮጀክት የሚገኙትን ንብረቶች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ  ከተገለፅበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ  የሥራ ቀናት በሥራ ሰዓት  በመገኘት መጎብኘት ይችላሉ፡፡

ጨረታው በጋዜጣ  በወጣ በ 10ኛው ቀን  ከሰዓት በኃላ 10፡00 ላይ ይዘጋል፡፡

ጨረታው በተዘጋ በነጋታው ከጠዋቱ 4 ሰዓት ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሠነድ በተሸጠበት ቢሮ ይከፈታል፡፡

በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋው 20% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የገንዘብ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) በማስያዝ በሰም በታሸገ ኤንቭሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

አሸናፊ የሆነው ተጫራቾች አሸናፊነቱ በተገለፅበት በ5 ቀናት ውስጥ የሚፈለግበትን  ክፍያ  ከፍሎ በአዲስ አበባ ላሉ ዕቃዎች በቀጣዩ አስራ አምስት ቀናት ውስጥ  ከአዲስ አበባ ውጭ ላሉ ዕቃዎች ደግሞ በ20 ቀናቶች /ሀያ  ቀናቶች / ውስጥ ያሸነፈውን ንብረት አውጥቶ መውሰድ ይኖርበታል፡፡ በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ  ቀርቦ ያሸነፈውን ዕቃ ካላወጣ ግን ኩባንያው ኃላፊነቱን አይወሰድም፡፡

በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቶች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጨረታው በተከፈተ ከ5 ቀናት በኃላ መውሰድ ይችላሉ፡፡

“ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ መሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡”

አድራሻ፡-ከአያት አደባባይ ወደ ጣፎ በሚወስድ መንገድ 200 ሜ ገባ ብሎ ጌት ህንፃ 5ኛ ፎቅ             ስልክ ቁ፤-ስልክ ቁ፡-011-6-62-63-57          ፋል ጠቅላላ ስራ ተራጭ

  “ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ መሉ የመሠረዝ መብቱ የተመበቀ   የተጠበቀ ነው፡፡”