አቢሲንያ ባንክ ሲገለገልባቸው የነበሩትን የተለያዩ 10 መኪናዎችን እና 7 ሞተር ሳይክሎችን በድምሩ 17 ተሽከርካሪዎችን እና 1 የተሽከርካሪ ቅሪት አካል በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Abissiniya-Bank-3

Overview

 • Category : Spare Parts Sale & Supply
 • Posted Date : 04/17/2022
 • Phone Number : 0115580706
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 04/27/2022

Description

ቢሲንያ ባንከ አ.ማ.

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር አባ/አሎመ/08/2022

አቢሲንያ ባንክ ሲገለገልባቸው የነበሩትን የተለያዩ 10 መኪናዎችን እና 7 ሞተር ሳይክሎችን በድምሩ 17 ተሽከርካሪዎችን እና 1 የተሽከርካሪ ቅሪት አካል በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

 • ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችንና የተሽከርካሪ ቅሪት አካሉን ከሰኞ መጋቢት 19 ቀን 20014 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ማክሰኞ ሚያዚያ 18 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ሜክሲኮ ከፊሊፕስ ሕንጻ ከፍ ብሎ ከፌደራል ፖሊስ ዋ/መ/ቤት ጎን በሚገኘው የባንኩ ትራንስፖርት አስተዳደር ግቢ ውስጥ በሥራ ሰዓት ብቻ በመገኘት ማየት ይቻላል፡፡
 • ስለ አሻሻጡ የተዘጋጀውን ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን የጨረታ ሠነድ በየትኛውም የአቢሲንያ ባንክ ቅርንጫፍ በሒሳብ ቁጥር PL54039 ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ ከከፈሉ በኋላ ከመጋቢት 19 ቀን 20014 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 19 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ ሦስት (03፡00) ሠዓት ድረስ የከፈሉበትን ደረሰኝ በመያዝ ሜክሲኮ ከፊሊፕስ ሕንጻ ከፍ ብሎ ከፌደራል ፖሊስ ዋ/መ/ቤት ጎን በሚገኘው ከባንኩ ትራንስፖርት አስተዳደር ቢሮ በመገኘት መውሰድ ይችላል፡፡
 • ተጫራቾች ለሚጫረቱበትን ተሽከርካሪ የጨረታ መነሻ ዋጋ 25% (ሃያ አምስት በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ለአቢሲንያ ባንክ (BANK OF ABYSSINIA) በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 • ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ አሸናፊ ለሆኑት ከሚገዙት ዕቃ ክፍያ የሚታሰብ ሲሆን ተሸናፊ ለሆኑት ያስያዙት ገንዘብ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
 • የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥኖች ረቡዕ ሚያዚያ 19 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት ሁሉም በአንድ ላይ ይዘጋሉ፡፡
 • የጨረታው ሰነድ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሜክሲኮ ከፊሊፕስ ሕንጻ ከፍ ብሎ ከፌደራል ፖሊስ ዋ/መ/ቤት ጎን በሚገኘው የባንኩ ትራንስፖርት አስዳደር ግቢ ውስጥ ረቡዕ ሚያዚያ 19 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 04፡00 ላይ ይከፈታል፡፡
 • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115-58-07-06 /0115-58-32-14 ወይም 0973-07-12-12 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል፡፡

መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡