የተቀናጀ የቤተሰብ አገልግሎት ድርጅት ሲገለገልባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Overview

 • Category : Vehicle Sale
 • Posted Date : 04/17/2022
 • Phone Number : 0911433707
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 05/02/2022

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን ሲገለገልባቸው የነበሩ፤

 1. Toyota Land Cruiser 4WD (ላንድ ክሩሰር)
 2. Toyota Runner 4WD (ራነር)

ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-

 1. ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ንብረቶቹ በሚገኙበት አድራሻ ማለትም ሾላ ገበያ ወደ ሲግናል በሚወስደው መንገድ የትራፊክ መብራቱን ሳይሻገር ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ቤክማ ዳቦ ቤት አጠገብ በሚገኘው በድርጅቱ ዋና መ/ቤት ግቢ ውስት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 7፡30 ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ፡፡
 2. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) አሰርተው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ለአሸናፊዎች ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን፤ ለተሸናፊዎች የጨረታው ውጤት በፀደቀ በ3/ሦስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ይመለስላቸዋል፡፡
 4. ተጫራቾች የንብረቶቹን ዝርዝር የያዘው ሰነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ (Column) ስር የሚገዙትን ዋጋ በአሃዝና በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልጸው በታሸገ ኤንቨሎፕ (ፖስታ) ድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ነገር ግን የሚሰጡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጎኑ በተጫራቹ መፈረም አለበት፡፡
 5. ተጫራቾች ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታውን ሰነድ ማስገባት አለባቸው፡፡ በበአስረኛው ቀን ግን የጨረታ ሰነዱ የሚገባው እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ይሆናል፡፡
 6. አሸናፊ ተጫራጮች ጨረታውን ማሸነፋቸውን ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ ከ3-5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ገቢ በማድረግ በ10/አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ተሽከርካሪውን የመረከብ ግዴታ አለባቸው ይህ ካልሆነ ያስዙት ገንዘብ ወይም ሲፖኦ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
 7. ተጫራቾች ከድርጅቱ አስተዳደር ክፍል የተሽከርካሪዎችን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ብር 150.00/አንድ መቶ ሃምሣ ብር/ እየከፈሉ ማስታወቂያው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15/አስራ አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናቶች ድረስ መግዛት የሚችሉ ሲሆን፤ በአስራ አምስተኛው ቀን ግን ሰነዱ የሚሸጠው እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ይሆናል፡፡
 8. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15/አስራ አምስት/ የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ15ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን 4፡30 ተጫራቾቹ ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ዋና መ/ቤት ይከፈታል፡፡
 9. ተጫራቾች ስለአሻሻጡ ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታው ሰነዱ ጋር ከተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
 10. ድርጅቱ ለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0911-43-37-07 011-8-69-97-250920-04-39-13  እና 011-8-12-27-73 መደወል ይቻላል፡፡

የተቀናጀ የቤተሰብ አገልግሎት ድርጅት