ጉድ ኔበርስ ኢትዮጵያ ደረቅ የልብስ ሳሙና 250 ግራም፤ ፈሳሽ የጸጉር ቅባት 330 ሚ.ሊ ሊትርና ቫዝሊን 100 ግራም በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Good-Neighbors-logo-1

Overview

 • Category : Purchases
 • Posted Date : 04/17/2022
 • Phone Number : 0115578614
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 04/26/2022

Description

 የንፅህና መጠበቂያ እቃዎች ግዢ የጨረታ ማስታወቂያ

  የጨረታ ቁጥር (BID GNE /09/2014

ጉድ ኔበርስ ኢትዮጵያ መንግሰታዊ ያልሆነ ለትርፍ ያልተቋቋመ አለምአቀፋዊ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን፣  ለድርጅቱ ተጠቃሚዎች የሚሆን ደረቅ የልብስ ሳሙና 250 ግራም፤ ፈሳሽ የጸጉር ቅባት 330 ሚ.ሊ ሊትርና ቫዝሊን 100 ግራም በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታዉ እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡

.  የእቃዉ አይነት መለኪያ ብዛት
1 ፈሳሽ የፀጉር ቅባት 330 ሚሊ ሊትር በቁጥር 20,572
2 ቫዝሊን 100 ግራም በቁጥር 35,184
3 ደረቅ የልብስ ሳሙና  250 ግራም በቁጥር 82,288

 

ተጫራቾች ሰነዱን ከዋናው መ/ቤታችን በሥራ ሰዓት መግዛት የምትችሉ ይሆናል፡፡

የጨረታ ሰነድ መግዣ ዋጋ 20ዐ.ዐዐ/ሁለት መቶ ብር/ ብቻ፡፡

 1. ተወዳዳሪዎች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/፣የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ማረጋገጫ /ክሊራንስ/፣የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 2. ጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 /ሰባት/ ተከታታይ የስራ ቀናት ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ልደታ ክ/ከተማ ባልቻ ሆስፒታል ጀርባ አህመድ የገበያ ማዕከል 5ኛ ፎቅ በሚገኘው ከዋናው መ/ቤታችን በሥራ ሰዓት የማይመወስ ብር 200 / ሁለት መቶ ብር  / በመክፈል ከፋይናንስ ክፍል መውሰድ ይችላል፡፡
 3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከቀረበው ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተመሰከረ ሲ.ፒ.ኦ ብቻ በድርጅቱ ስም በማሰራት ከጨረታ ዶክመንቱ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸዉን በሁለት ፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናልና ኮፒ ብለው በመፃፍ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ በግልጽ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በመሙላት በግርጌው ስም፣ፊርማና የድርጅታቸውን ማህተም በማኖር ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ7ኛው ቀን ማለትም ሚያዚያ 18 ቀን 2014 ዓ.ም በጠዋቱ 4፡ዐዐ ሰዓት ተዘግቶ 4፡3ዐ ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
 5. ድርጅቱ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
 6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን እቃ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

     አድራሻ፡-  ልደታ ባልቻ ሆስፒታል ጀርባ አህመድ የገበያ ማዕከል 5ኛ ፎቅ

      ለበለጠ መረጃ ፡ – በስልክ ቁጥር  +251 115578614