ተጂ ኢንተርናሽናል ኃ/የተ/የግ/ማህበር ያገለገሉ መለስተኛ ቫን የጭነት ተሽከርካሪዎችንና አነስተኛ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Vehicle Sale
 • Posted Date : 04/17/2022
 • Phone Number : 0116465911
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 05/02/2022

Description

ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ

 ተጂ ኢንተርናሽናል ኃ/የተ/የግ/ማህበር ያገለገሉ መለስተኛ ቫን የጭነት ተሽከርካሪዎችንና አነስተኛ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

 1. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከድርጅቱ ዋና መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 እየቀረቡ መውሰድ ይችላሉ፡፡
 2. ተጫራቾች ተሽከርካሪዎቹን ዘወትር በስራ ሰዓት ጃክሮስ አደባባይ አካባቢ ወደ አምባሳደር ልብስ ስፌት ፋብሪካ መሔጃ በሚገኘው የድርጅቱ መጋዘን በመገኘት መመልከት ይችላሉ ፡፡
 3. ማንኛውም በጨረታው ላይ የሚሳተፉ ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ ለመግዛት ባቀረቡት ዋጋ 10% የጨረታ ማስከበሪያ /BID BOND/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከዋናው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 4. ተጫራቾች ሊገዙ የሚፈልጉትን ተሽከርካሪ የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ዶክመንቱ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ፖስታ ውስጥ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በድርጅቱ ዋና መ/ቤት እንግዳ መቀበያ ቢሮ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 5. ጨረታው 29/8/2014 ከቀኑ 10:00 ሰዓት ይዘጋል ፡፡
 6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅታችን ዋና መ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ 02/09/2014 .. ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ካልተገኙ ጨረታው በድርጅቱ የሚመለከታቸው ባለሙያዎችና ኃላፊዎች አማካይነት የሚከፈት ይሆናል ፡፡
 7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ተእታ /VAT¼ ያካተተ መሆን ይኖርበታል ፡፡
 8. ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ካቀረቡት ዋጋ አንሶ ከተገኘ ከጨረታው ይሰረዛሉ ፡፡
 9. የጨረታ ዋጋ ቅፅ ላይ ሲሞላ ስርዝ ድልዝ እና አሻሚነት ያለው የቁጥር አፃፃፍ ተቀባይነት የለውም ፡፡
 10. የጨረታ አሸናፊዎች ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ቀናት ውስጥ ጨረታ ያሸነፉበት ዋጋ ሙሉ በሙሉ ከፍለው ማጠናቀቅ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ የማይሆን ከሆነ የጨረታ ኧሸናፊው የጨረታ ማስከበሪያ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ለ2ኛ ጨረታ አሸናፊ የሚሰጥ ይሆናል ፡፡
 11. የጨረታ አሸናፊዎች ክፍያ በፈፀሙ በ10 ቀናት ውስጥ ተሽከካሪዎቹን በራሳቸው ትራንስፖርትና ወጪ ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡
 12. የጨረታ ተሳታፊ ሆነዉ ጨረታዉን ላላሸነፉ ተጫራቾች በጨረታ ያስያዙት የጨረታ ማሰከበሪያ /BID BOND/ ወዲያዉኑ ተመላሽ የሚደረግ ሲሆን በጨረታ ላሸነፉት ደግሞ ከግዥዉ ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸዉ ይሆናል፡፡
 13. የስም ማዛወሪያ ቴምብር፤ቀረጥ፤የፍርድ ቤት ፤የመንገድ ትራንስፖርትና ሌሎች ወጪዎችን ገዥ ይከፍላል፡፡
 14. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡-

  አድራሻ፡- ተጂ ኢንተርናሽናል ኃ/የተ/የግ/ማህበር

 ከገርጂ መብራት ኃይል ወደ ሰሃሊተምህረት ቤተክርስቲያን በሚወስደው መንገድ ከሜታ ቢራ ማከፋፈያ ገባ ብሎ ካኪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር አጠገብ

 ስልክ፡- 011 646-5911/12/13

           0911679312