የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለተበዳሪዎች ለሰጠው የብድር ገንዘብ አመላለስ በመያዣነት የያዘውን ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/98 እና 1147/11 በተሰጠው ስልጣን መሠረት በግልፅ/ሐራጅ ባሉበት ሁኔታ ለመሸጥ ይፈልጋል::
Overview
- Category : House & Building Foreclosure
- Posted Date : 04/20/2022
- Phone Number : 0115244269
- Source : Reporter
- Closing Date : 05/24/2022
Description
የሐራጅ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለተበዳሪዎች ለሰጠው የብድር ገንዘብ አመላለስ በመያዣነት የያዘውን ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/98 እና 1147/11 በተሰጠው ስልጣን መሠረት በግልፅ/ሐራጅ ባሉበት ሁኔታ ለመሸጥ ይፈልጋል::
ተ.ቁ | የተበዳሪው ስም | የንብረት አድራሻ | የንብረት ዝርዝር | የቦታ ስፋት | የሃራጁ መነሻ
ዋጋ (በብር) |
የሐራጁ
ደረጃ |
የሐራጁ ቀንና
ሠዓት |
1 | ኪዳኔ ወ/ማርያም እርሻ ልማት ኢንተርፕራይዝ
|
ጋምቤላ ክልል ፣
አኝዋሃ ዞን ጎግ ወረዳ፣ አተቲ ቀበሌ |
ግንባታዎች፤ የእርሻ መሳሪያዎች እና የመሬት ልማት | 1,505 ሄክታር | 19,375,630.60
(አስራ ዘጠኝ ሚሊዮን ሶስት መቶ ሰባ አምስት ሺህ ስድስት መቶ ሰላሳ ብር ከስልሳ ሳንቲም) |
የመጀመሪያ
ሐራጅ |
ግንቦት 16 ቀን 2014 ዓ.ም
ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት |
2 | ቲ..ኤል.ኤፍ አግሮ ኢንደስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
|
ጋምቤላ ክልል ፣
አኝዋ ዞን ጋምቤላ ወረዳ፣ ሶለን ቀበሌ |
ግንባታዎች፤ ተሽከርካሪ፣ የእርሻ መሳሪያዎች እና መሬት ልማት | 1,268 ሄክታር | 21,282,455.83
(ሃያ አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሰማኒያ ሁለት ሺህ አራት መቶ ሃምሳ አምስት ብር ከሰማኒያ ሶስት ሳንቲም) |
የመጀመሪያ
ሐራጅ |
ግንቦት 17 ቀን 2014 ዓ.ም
ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት |
3 | አለምገነት ንግድና ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ ማህበር | አዲስ አበባ ከተማ
አስተዳደር፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ፣ ወረዳ 12 |
ግንባታዎች፤የመስሪያ ማሽኖች፣ተሽከርካሪዎች፣ጥሬ እቃ እና ተረፈ- ምርቶች |
3,967 ካ.ሜ |
213,818,338.64 (ሁለት መቶ አስራ ሶስት ሚሊዮን ስምንት መቶ አስራ ስምንት ሺህ ሶስት መቶ ሰላሳ ስምንት ብር ከ64/100) |
ሁለተኛ ሐራጅ |
ግንቦት 17 ቀን 2014 ዓ.ም
ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት |
ማሳሰቢያ ፤
- ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ 25 በመቶ በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.ኦ/ ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፤
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 /በአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡
- ሐራጁ የሚካሄደው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው፣ ተበዳሪው እና የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ተወካዮች በተገኙበት በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ንብረቶቹ በሚገኙበት አድራሻ ነው :: በሐራጁ ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.ኦ/ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
- 15% የተጨማሪ እሴት ታክስና ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰነ ክፍያዎችን፣ የስም ማዛወሪያ ክፍያን ጨምሮ ገዢው ይከፍላል፤
- አንዳንድ የድርጅቱ ተሽከርካሪዎች፣የእርሻ መሣሪያዎች፣ወዘተ የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለባቸው ስለሆኑ ገዢው የቀረጥ ነጻ መብት ሊኖረው አሊያም በመንግስት የሚፈለገውን ቀረጥ ለመክፈል ይገደዳል ::
- ባንኩ ለሽያጭ የቀረቡትን ንብረቶች የሚሸጠው ከተቻለ ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ ሲሆን አሸናፊው በባንኩ ብድር ፖሊሲ መሠረት አስፈላጊውን መስፈርቶች ካሟላና የፕሮጀክቱን ሥራ የሚያስቀጥል ከሆነ ንብረቱን በከፊል ብድር ለመግዛት መጠየቅ ይችላል:: ነገር ግን በከፊል ብድር ለመግዛት የጨረታ አሸናፊው በራሱ ስም ወይም እራሱ 10%/አስር በመቶ/ ወይም ከዚያ በላይ የአክሲዮን ባለድርሻ የሆነበት የንግድ ማህበር ከግብር፤ከታክስና ከሌሎች ማናቸውም ዕዳዎች ነፃ መሆኑን ከሚመለከታቸው አካላት ማስረጃ በማቅረብ እንዲሁም ምንም ዓይነት የዕዳ ይከፈለኝ ጥያቄ ያልቀረበበት መሆን አለበት፡፡
- ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃን በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዋና መ/ቤት ታወር ሁለት ሦስተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኘሮጀክት ማገገሚያና ብድር ማስመለስ ዳይሬክቶሬት I በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-524-42-69 ደውሎ ማግኘት ይቻላል ወይም ከባንኩ ድህረ ገጽ dbe.com.et. ማግኘት ይቻላል፡፡ ንብረቱን ለመጎብኘት የሚፈልጉም ካሉ ከዳሬክቶሬቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጐብኘት ይቻላል፤
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ሐራጁን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ