ኢማጂን ዋን ዴይ ኢንተርናሽናል ኦርጋናይዜሽን /imagine1day/ በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ዞን ሁለት የመጀመርያ ደረጃ ት/ቤቶችን ለመገንባትከክልሉ መንግስት ጋር በገባዉ የፕሮጀክት ውል መሰረት፤ የሚከተሉትን ስራዎች በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

Imagin-Day-One-Logo-reportertenders

Overview

 • Category : Construction Service & Maintenance
 • Posted Date : 04/25/2022
 • Phone Number : 0118697258
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 05/05/2022

Description

የት/ቤት ግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር:- I1D/BETE/01/2022

        ኢማጂን ዋን ዴይ ኢንተርናሽናል ኦርጋናይዜሽን /imagine1day/ የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ የውጭ በጎ አድራጎት ድርጅት በኦሮሚያ, በአማራ፣ በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል፣ በትግራይ, እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በትምህርት ጥራት ማሻሻል ሥራ ላይ የበኩሉን አስተዋፅኦ እየሰራ ይገኛል፡፡

በዚሁ መሰረት ድርጅታችን በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ዞን ሁለት የመጀመርያ ደረጃ ት/ቤቶችን ለመገንባትከክልሉ መንግስት ጋር በገባዉ የፕሮጀክት ውል መሰረት፤ የሚከተሉትን ስራዎች በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

የትምህርት ቤቶች ግንባታ ስራ

 1. በሰሜን ወሎ ዞን በዋድላ ወረዳ መለይ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ሁለት ብሎክ እያንዳንዱ አራት የመማርያ ክፍሎችን የያዘ, አንድ የስነ- ንጵህና ጤና አጠባበቅ ክፍል እና ሁለት ባለ ስምንት ክፍል ሽንት ቤቶች፡፡
 1. በሰሜን ወሎ ዞን በራያ ቆቦ ወረዳ ጫሮ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ሁለት ብሎክ እያንዳንዱ አራት የመማርያ ክፍሎችን የያዘ, አንድ የስነ- ንጵህና ጤና አጠባበቅ ክፍል እና ሁለት ባለ ስምንት ክፍል ሽንት ቤቶች፡፡

ስለሆነም

 • ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረበ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
 • ለግንባታ ደረጃ 5 እና ከዛ በላይ የግንባታ ፍቃድ ያላቸው፡፡
 • ለግንባታ በገጠር ቢያንስ አምስት ተመሳሳይ ፕሮጆክቶችን ሰርቶ በአግባቡ ያጠናቀቀ ፡፡
 • ተጫራቾች ስለ ጨረታው የሚገልፀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) እና የታደሰ ንግድ ፍቃዳችሁን ከስራ ልምዳችሁ ጋር በመያዝ አዲስ አበባ፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ ኢምፔሪያል አካባቢ ልዩ ስሙ 24 ከ ሚክሲኮ ኤምባሲ አጠገብ ከሚገኝው የድርጅታችን ዋና መ|ሪያ ቤት ከ ሚያዚያ 17 እስከ ሚያዚያ 27 2014 ዓ/ም እስክ ጠዋት 4:30 ድረስ ባለው የስራ ሰዓት የጨረታ ሰነዶችን መግዛት ይችላሉ፡፡
 • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና ባንክ ጋራንቲ (Bank Guarantee) ወይንም በባንክ የተረጋገጠ CPO ለ180 ቀን የሚቆይ ከሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ከቫት በፊት 5% በተጨማሪ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 • ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ፋይናንሸያል እና ቴክኒካል ፐሮፖዛል ዋናውን ከአንድ አንድ ኮፒ በማድረግ እያንዳንዱን ሰነድ በታሸገ ኢንቨሎፕ እና ሁሉንም ሰነዶች በትልቅ ኢንቨሎፕ በማሽግ ሚያዚያ 27 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 • ጨረታው ሚያዚያ 27 ቀን 2014 ዓ.ም 8:00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደሴ ከተማ ሆጤ ክፍለ ከተማ አገር ግዛት ቀበሌ ከመርሆ ግቢ ፊት ለፊት ከሚገኝው የኢማጅን ዋን ዴይ የደቡብ ወሎ ዞን ማስተባበሪያ መ|ሪያ ቤት ይከፈታል፡፡
 • ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 አድራሻ: -ኢማጂን ዋን ደይ ኢንተርናሽናል ኦርጋናይዜሽን

 የቀጥታ ስልክ ቁጥር 011 869 7258

 ፓ.ሳ.ቁ   170910