የካራ-አሎ ቄራ ኃ.የተ.የግ.ማ አስተዳር የኢንደስትሪ ፍሳሽ ማጣሪያ ግንባታን ገንብተው ለማጠናቀቅ ፍላጎት ያላቸው እና ብቁ የሆኑ ከGC-5/BC-5/WWC-5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የሥራ ተቋራጮችን ይጋብዛል።

Overview

 • Category : Construction Service & Maintenance
 • Posted Date : 05/01/2022
 • Phone Number : 0911541834
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 05/21/2022

Description

የካራ-አሎ ቄራ ኃ.የተ.የግ.ማ አስተዳር በቀረበው ዝርዝር ሥዕላዊ መግለጫዎች እና የዲዛይን ምክሮች መሠረት የኢንደስትሪ ፍሳሽ ማጣሪያ ግንባታን ገንብተው ለማጠናቀቅ ፍላጎት ያላቸው እና ብቁ የሆኑ ከGC-5/BC-5/WWC-5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የሥራ ተቋራጮችን ይጋብዛል። “፣ቦታው አርባ ቁጥር ማዞሪያ በሚገኘው  ካራ አሎ ቄራ፣ የካ ክፍለ ከተማ አዲስ አበባ።

በዚህ መሠረት ተጫራቾች የንግድ ምዝገባ ፈቃድ ያላቸው፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የታክስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት እና ከተፈቀደለት አካል የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ያላችሁ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።

 1. የካራ-አሎ ቄራ ኃ.የተ.የግ.ማ ከፎረም ዎርክ እና ከዚሁ ጋር ተዛማጅ ከሆኑ እቃዎች በስተቀር ሁሉንም የግንባታ ግብዓቶች ያቀርባል፡፡
 2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 1,000.00 ብር (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል ከካራ-አሎ አባቶር ኃ/የተ/የግ/ማህበር አስተዳደር ጽ/ቤት መግዛት ይችላሉ። ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከታች በተጠቀሰው አድራሻ ማግኘት ይችላሉ።
 3. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ብር 120,000.00 (አንድመቶ ሃያ ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ፣ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ ለተጠቀሰው መ/ቤት ማቅረብ አለባቸው።
 4. የፋይናንስ አቅርቦት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እንደ “ፋይናንሻል ኦሪጅናል” እና “የፋይናንስ ቅጂ” በተሰየሙ ኤንቨሎፖች መቅረብ አለበት። እንዲሁም የቴክኒካል አቅርቦቱ በተለየ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ “ቴክኒካል ኦሪጅናል” እና “ቴክኒካል ኮፒ” ተብሎ በግልፅ መፃፍ አለበት። ሁሉም በሰም የታሸጉ ኤንቨሎፖች የቴክኒክ አቅርቦት፣ የፋይናንሺያል አቅርቦት እና ሲፒኦ በፊርማ እና በሰም በታሸገ የውጪ ኤንቨሎፕ ውስጥ ተካትተው ለካራ-አሎ አባቶር ኃ.የተ.የግ.ማ አስተዳደር ይላካሉ።
 5. ጨረታው በ20ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ካራ-አሎ አባቶር፣ አዲስ አበባ።
 6. ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ይካሄዳል።
 7. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተጠየቁትን አስፈላጊ ዝርዝሮች በሙሉ ለመሙላት የጨረታ ሰነዱን በደንብ እንዲያነቡ ይመከራሉ።
 8. ተጫራቾች በቄራው አስተዳዳሪ የተዘጋጀውን የግንባታ ቦታ እንዲጎበኙ ይመከራሉ።
 9. ተጫራቾች በጨረታው ውስጥ የተጠየቁትን አስፈላጊ ዝርዝሮች በሙሉ መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
 • ካራ-አሎ ቄራ ኃ.የተ.የግ.ማ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ካራአሎ ቄራ .የተ.የግ.

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ስልክ– +09 11 54 18 34

     +09 11 63 70 08