ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር የፈረሰኞች ስፖርት ባር ለደጋፊዎች፣ ለአባላትና ለህብረተሰቡ የምግብና መጠጥ አገልግሎት ለመስጠት በሚችል መልኩ የተደራጀ ስለሆነ ከዚህ በታች የተመለከቱትን መመዘኛዎች የሚያሟሉና አቅሙና ፍላጎቱ ያላቸውን ድርጅቶች ሁሉ በጨረታ አወዳደሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Catering Service
 • Posted Date : 05/01/2022
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 05/31/2022

Description

የጨረታ ሰነድ ዝግጅት ጥሪ

ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ንግድ ሥራ ኮሌጅ አጠገብ ኖከ ነዳጅ ማደያ ጎን የሚገኘውንና ባንድ ጊዜ 100 የሰው ኃይል ለማስተናገድ የሚችለውን እና በተለምዶ ለገሀር ሼመንደፈር በሚባለው አካባቢ ያለው የፈረሰኞች ስፖርት ባር ለደጋፊዎች፣ ለአባላትና  ለህብረተሰቡ የምግብና መጠጥ አገልግሎት ለመስጠት በሚችል መልኩ የተደራጀ ስለሆነ ከዚህ በታች የተመለከቱትን መመዘኛዎች የሚያሟሉና አቅሙና ፍላጎቱ ያላቸውን ድርጅቶች ሁሉ በጨረታ አወዳደሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

 1. የምግብና መጠጥ ቤቶችን በመምራትና በማስተዳደር ከአምስት ዓመት ያላነሰ ልምድ ያለው ይህንንም በጽሁፍና በማስረጃ ማቅረብ የሚችል
 2. ተጫራች በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ ዋና ምዝገባና የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችል፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት)፣ እና የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው
 • ድርጅቱን ለመምራትና ለማስተዳደር በቂ የፋይናንስ ምንጭ ያለውና ማስረጃ የሚያቀርብ
 • ማንኛውም ተጫራች ብር 200 የማይመለስ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከስፖርት ማህበሩ ጽ/ቤት መግዛትና መወዳደር ይችላል፡፡
 • የጨረታ ሰነዱን ከስፖርት ማኅበሩ ጽ/ቤት ዘወትር በስራ ሰዓት ከ ሚያዝየያ 24 ቀን  2014 ዓ.ም ጀምሮ መግዛት ይችላል፡፡
 • ተጫራች /ድርጅት ያዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሚያዝያ 24 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ግንቦት 23 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 6 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የስፖርት ማኅበሩ ባዘጋጀው ሳጥን ውስጥ መክተት አለበት ጨረታው ግንቦት 24 ቀን 2014 አ. ም. ከጠዋቱ በ4 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በስፖርት ማኅበሩ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡
 • ከጨረታው መግቢያ ቀንና ሰዓት በኋላ ዘግይተው የሚቀርቡ የጨረታ ሰነዶች ሁሉ ተቀባይነት የላቸውም
 • የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተበት ዕለት ጀምሮ ለ90 ቀናት የፀና ይሆናል፡፡
 • የስፖርት ማኅበሩ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

አድራሻ

ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር

ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ደብረዘይት መንገድ ጠመንጃ ያዥ

ኖክ ነዳጅ ማደያ ህንፃ 1ኛ ፎቅ

አዲስ አበባ