ዳሽን ባንክ አ.ማ. ዝርዝራችው ከዚህ በታች የተገለፁትን ያገለገሉ የባንኩን ተሸከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳደሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Dashen-Bank-Logo-Reportertenders-5

Overview

  • Category : Other Sale
  • Posted Date : 05/01/2022
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 05/24/2022

Description

ግልፅ ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች

ጨረታ ማስታወቂያ

ዳሽን ባንክ አ.ማ. ዝርዝራችው ከዚህ በታች የተገለፁትን ያገለገሉ የባንኩን ተሸከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳደሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ  የተሸከርካሪው ዓይነት የሰሌዳ ቁጥር የተሰራበት ዘመን የጨረታ መነሻ ዋጋ በብር
1 ቼቭሮሌት ሰቨርቫን ተሸከርካሪ 3-06727 1994 420,000.00
2 ቼቭሮሌት አቪዮ አውቶሞቢል 3-24138 2004 310,000.00
3 አይሱዙ ትሩፐር 4WD 3-02565 2001 630,000.00
4 ፎርድ አቬረስት 4WD 3-37624 2006 811,990.00
5 ፎርድ አቬረስት 4WD 3-39417 2006 1,220,000.00

የሞተር ሳይክል

ተ.ቁ የተሸከርካሪውዓይነት የሰሌዳ ቁጥር የተሰራበት ዘመን የጨረታ መነሻ
1 ሱዙኪ 3-0146 2007 35,000.00
2 ያማሃ 3-0330 2000 72,964.00
3 ያማሃ 3-0096 2003 72,964.00

ተጫራቾች ለጨረታው ከመቅረባቸው በፊት ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል ፡፡

  1. ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ ለመኪና 20 በመቶ እንዲሁም ለሞተር ብስክሌት ብር 5,000 (ብር አምስት ሺህ) የጨረታ ማሰረከቢያ (ቢድ ቦንድ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) በጨረታው ዕለት ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
  2. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ዋጋ በ15 ቀናት ውስጥ ለባንኩ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ገቢ የማያደርግ ተጫራች ጨረታው ተሠርዞ ለጨረታው ማሰከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ አይመለስለትም፡፡
  3. የተጠቀሰው የጨረታ መነሻ ዋጋ ቫትን አያካትትም በመሆኑም የጨረታው አሸናፊ የተጨማሪ እሴት ታክስን ዋጋ ጨምሮ ይከፍላል፡፡
  4. ተጫራቾች ተሸከርካሪዎቹን ባሉበት ሁኔታ በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት 3ኛ ቤዝመንት(ግራውንድ) የመኪና ማቆሚያ ቦታ በአካል በመገኘት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 15 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ ባሉት ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እሰከ 11፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ ባለው ጊዜ መመልከት ይቻላል፡፡
  5. የጨረታው መክፈቻ ቀን ግንቦት­­­ 16/2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ሲሆን፤ ቦታውም አዲስ አበባ ልደታ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው የዳሽን ባንክ ሕንፃ 4ኛ ፎቅ ላይ ይሆናል፡፡
  6. ባንኩ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል ጨረታውን የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡