አንፕካን ኢትዮጵያ የድርጅቱ ንብረት የሆኑትን 4 መኪናዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ANPPCAN-Ethiopia-logo

Overview

 • Category : Vehicle Sale
 • Posted Date : 05/01/2022
 • Phone Number : 0115505202
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 05/18/2022

Description

የመኪና ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ

አንፕካን ኢትዮጵያ የድርጅቱ ንብረት የሆኑትን 4 መኪናዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት ማንኛውም ተጫራች ጨረታዉ በሚካሄድበት ቀን መኪናዎቹ በሚገኙበት ቦታ በመገኘት በጨረታው ተወዳድሮ መኪናዎቹን መግዛት ይችላል፡፡

 • የመኪናዎቹ አጠቃላይ መረጃ፤

1ኛ/ ደብል ካቢን ፒክ አፕ ቶዮታ መኪና ሞዴል LN106EPRMRS የታርጋ ቁጥሩ ኮድ 35-1017 የሆነውን ያገለገለ መኪና የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 250,000.00

2ኛ/ ደብል ካቢን ፒክ አፕ ቶዮታ መኪና ሞዴል LN166 የታርጋ ቁጥሩ ኮድ 35-1835 የሆነውን ያገለገለ መኪና የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 500,000.00

3ኛ/ ደብል  ካቢን ፒክአፕ ሚትሱቢሺ መኪና ሞዴል K34TSUNTJL የታርጋ ቁጥሩ ኮድ 35-1754 የሆነውን ያገለገለ መኪና የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 500,000.00

4ኛ/ ቶዮታ ላንድ ክሩዘር  ሞዴል HZJ80L  የታርጋ ቀጥሩ ኮድ 35-1117 የሆነውን ያገለገለ መኪና የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 700,000.00 ባሉበት ሁኔታ ለማሽጥ ይፈልጋል፡፡

 • የመኪናዎቹን ሁኔታ ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች መኪናዎቹ ባሉበት የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ጉርድ ሾላ ከአትሌቲክስ ፌደሬሽን ህንፃ እና ከበሻሌ ሆቴል መካከል ብርሃን ኢንተርናሽናል ባንክ ያለበት ህንፃ ግቢ ውስጥ እንዲሁም የታርጋ ቁጥሩ ዕድ 35-1017 የሆነው መኪና ጎንደር ከተማ ቱሪዝም ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በመገኘት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት  ማለትም ከሚያዝያ 24 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ግንቦት 9 ቀን 2014 ዓ.ም. ዘወትር በስራ ሰዓት ጠዋት ከ3፡00 – 5፡00 ከሰዓት ከ8፡00 – 10፡00 ሰዓት ማየት ይችላሉ፡፡
 • ተጫራቾች ለሚጫረቱበት መኪና የመነሻ ዋጋ 2% (ሁለት በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) አሰርቶ በጨረታው ቀን ይዞ በመቅረብ መመዝገብ ይችላሉ፡፡
 • ጨረታው ግንቦት 9 ቀን 2014 ዓ.ም. ከምሽቱ 11፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ግንቦት 10 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት መኪኖቹ በሚገኙበት በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት የሚካሄድ ይሆናል፡፡
 • በተራ ቁጥር 1ኛ ላይ የተጠቀሰው ቶዮታ ፒክ አፕ ደብል ካቢን የታርጋ ቁጥሩ 35-1017 የሆነው መኪና ጨረታ የሚከፈተውም ግንቦት 10 ቀን 2014 ዓ.ም. ዓ.ም ከጠዋቱ በ 4፡00 ሰዓት ጎንደር ከተማ ዋልያ ካፕራ ሆቴል አጠገብ በሚኘው የአንፕካን ኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ውስጥ ነው፡፡
 • በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከሚያዝያ 24 ቀን 2014 እስከ ግንቦት 9 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ  የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ከአንፕካን-ኢትዮጵያ ዋና መ/ቤት ወይም ከአንፕካን ጎንደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት (የታርጋ ቁጥሩ 35-1017) ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት  ይችላሉ፡፡
 • ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ ባለዉ የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በመሙላት ዋናዉንና ኮፒዉን በተለያዩ ፖስታ በማደረግና ሁለቱን ፖስታዎች በአንድ ላይ በሌላ ፖስታ ዉስጥ አድረግዉ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ለዚሁ በተዘጋጀዉ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
 • ድርጅቱ የጨረታዉን አሸናፊ በደብዳቤ የሚያሳዉቅ ሲሆን ዉጤቱን ለተሳታፊዎች በግልጽ በማስታወቂያ ቦርድ በመለጠፍ የሚያሳዉቅ ይሆናል፡፡
 • የጨረታው አሸናፊ ያሸነፉትን ተሸከርካሪ ሙሉ ክፍያ ጨረታውን ማሸነፉንና መኪናዉን እንዲረከብ በደብዳቤ ድርጅቱ ካሳወቀበት ማግስት ጀምሮ በሚቆጠር በ15 ቀናት ውስጥ ለድርጅቱ ገቢ በማድረግ መኪናውን መረከብ ይኖርበታል፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ግን ለጨረታው ያስያዘው ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ጨረታው ተሰርዞ ለሐራጅ የሚቀርብ ይሆናል፡፡ በጨረታው ተሳትፈው ላላሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
 • የጨረታው አሸናፊ ለስም ማዛወሪያና ሌሎች ተጓዳኝ ወጪዎችን በሙሉየ ሚሸፍን ይሆናል፡፡
 • ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 • ለተጨማሪ መረጃ አዲስ አበባ በስልክ ቁጥር 0115505202/01115502222 እንዲሁም ጎንደር በስልክ ቁጥር 0581119663 ወይም 0582112938 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አንፕካን ኢትዮጵያ