ሀገረሰብ ሪል እስቴት አ.ማ ለሚያስገነባው 2B+G+15 ቅይጥ ህንፃ ግንባታ ከታች በሰንጠረዥ በቀረበው መልኩ የመስኮት ደፍ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

Overview

  • Category : House & Building Construction
  • Posted Date : 05/04/2022
  • Phone Number : 0930601161
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 05/13/2022

Description

የመስኮት ደፍ (Window Sill) ግዥ ጨረታ

ድርጅታችን ሀገረሰብ ሪል እስቴት አ.ማ ለሚያስገነባው 2B+G+15 ቅይጥ ህንፃ ግንባታ ከታች በሰንጠረዥ በቀረበው መልኩ የመስኮት ደፍ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም እቃውን ለመሸጥ ህጋዊ ፍቃድ (የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የገቢዎች ክሊራንስ) እና አቅሙ ያለው ድርጅት የጨረታ ሰነዱን ሪቼ አከባቢ ከሚገኘው ቢሯችን የማይመለስ ብር 500 በመክፈል መውሰድ ይችላል፡፡ ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ በሚቆጠሩ አስር ቀናት ውስጥ መመለስ ይኖርበታል፡፡ ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡

ተ.ቁ የስራው አይነት እና ስፋት ለመወዳደር የሚያስፈልጉ ሁኔታዎች
1 68.21 ካሬ Window Sill (የመስኮት ደፍ) አቅርቦት v  የሚቀርበው የመስኮት ደፍ ጥቁር ከለር ያለው እና ውፍረቱ 3ሳንቲም የሆነ ቡርኖስ እና ግሩቭ የተሰራለት እምነበረድ (3cm thick Black Marble) መሆን ይኖርበታል፤

v  ተጫራቹ የሚሰራበትን (ዋጋ የሰጠበትን) የመስኮት ደፍ ሳምፕል ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ ማስገባት ይኖርበታል፤

v  ተጫራቹ ለስራው የሚያስፈልገው ያህል በቂ የመስኮት ደፍ በእጁ ያለ (Sufficient available stock) እና በ 1ወር ጊዜ ውስጥ ሰርቶ ማስረከብ የሚችል መሆን ይኖርበታል፤

v  ተጫራቹ የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 ብር ሲ.ፒ.ኦ በአሰሪው ድርጅት ስም ማለትም HAGERESEB REAL ESTATE S.C አሰርቶ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት ይኖርበታል፤

v  ተጫራቹ የሚጫረትበትን የመስኮት ደፍ ልኬት ዝርዝር (Schedule) ከጨረታ ሰነዱ ጋር መውሰድ ይኖርበታል፤

አድራሻ፡ ከጨርቆስ ወደ ሪቼ በሚያስወጣው መንገድ ከማንዴላ የርቀት ትምህርት ዝቅ ብሎ ወረዳ 10 ጋር ሳይደርስ ዞዊ መካከለኛ ክሊኒክ አጠገብ፡፡

 ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡ 0930 601161፣ 0114 701360