ደቡብ ግሎባል አ.ማ. ለ2015 በጀት ዓመት መጋረጃ (Vertical Blind) ሥራ አገልግሎት ግዥ በመፈጸም ሕጋዊ የአገር ውስጥ ድርጅቶችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

Debub-global-Bank-Logo-reportertenders

Overview

 • Category : Purchases
 • Posted Date : 05/07/2022
 • Phone Number : 0115581204
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 05/23/2022

Description

ደቡብ ግሎባል ባንክ .

መጋረጃ (Vertical Blind) ሥራ አገልግሎት ግዥ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 01/22/23

 1. ደቡብ ግሎባል አ.ማ. ለ2015 በጀት ዓመት መጋረጃ (Vertical Blind) ሥራ አገልግሎት ግዥ በመፈጸም ሕጋዊ የአገር ውስጥ ድርጅቶችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
 2. የጨረታ ሰነዱን በባንኩ ዋና መ/ቤት በሚገኝበት ናሽናል ቢዝነስ ሴንተር ሕንጻ 11ኛ ፎቅ (ስታዲየም ኢትዮጵያ ሆቴል ጀምባ) ንብረትና ፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ ቢሮ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል እና የገቢ ደረሰኝ ይዞ በመቅረብ ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት 2፡ዐዐ እስከ 6፡ዐዐ ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ እንዲሁም ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
 3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በሚወስዱበት ወቅት የድርጅታቸውን የመስመር ስልክ እና የሞባይል ስልክ ቁጥር በትክክል እና ግልጽ በሆነ መልኩ መጻፋቸውን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡ በትክክልና ግልጽ ሆኖ ባልተጻፈ አድራሻ ምክንያት ጨረታውን በተመለከተ በስልክ ለሚተላለፍ መረጃ አለመድረስ ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም፡፡
 4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺ ብር) በሲ.ፒ.ኦ ወይም ቅድመ ሁኔታ በሌለው የባንክ ዋስትና መቅረብ ይኖርበታል፡፡
 5. ሁሉም ተጫራቾች ከግንቦት 15 ቀን 2014 ዓ.ም በፊት ወይም በእለቱ እስከ ጠዋቱ 4፡ዐዐ ሰዓት ድረስ በተራ ቁጥር 2 ላይ በተጠቀሰው አድራሻ በመገኘት ያዘጋጁትን ሰነድ ለጨረታ ሰነድ ማስገቢያ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸል፡፡
 6. ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 2 እስከ 5 የተጠቀሱትን ቅድመ ሁኔታዎች ሳያሟሉ ከቀሩ ከጨረታው ይሰረዛሉ፡፡
 7. ለመጫረት ፍላጎት ያላቸው ሕጋዊ ድርጅቶች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011 558 12 04 ወይም 011 531 81 56 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
 8. ባንኩ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊት የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡