የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት በአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ ለሰራተኞች የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ በጥሩ ቴክኒካዊና አካላዊ ሁኔታ ላይ የሚገኙና የ2010 እና ከዚያ በላይ ሞዴል የሆኑ ሁለት (2) ተሽከርካሪዎችን መከራየት ይፈልጋል፡፡

Defence-Construction-Enterprise-3

Overview

  • Category : Vehicle Rent
  • Posted Date : 05/09/2022
  • Phone Number : 0118960629
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 05/20/2022

Description

የተሽከርካሪ ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት በአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ ለሰራተኞች የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ፡-

  1. ከ 12 – 15 የመቀመጫ ወንበር ያለው (ሰርቪስና ሌሎች የሙሉ ቀን ስራዎች የሚሰራ) እና
  2. ከ 15- 24 የመቀመጫ ወንበር ጠዋትና ማታ ለሰርቪስ አገልግሎት ብቻ

በጥሩ ቴክኒካዊና አካላዊ ሁኔታ ላይ የሚገኙና የ2010 እና ከዚያ በላይ ሞዴል የሆኑ ሁለት (2) ተሽከርካሪዎችን መከራየት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም የዘመኑን ግብር የከፈላችሁ፣ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ በዘርፉ የተሰማራችሁ ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር (10) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ወሎ ሰፈር አምባሰል ህንጻ ፊት ለፊት ብራና ማተሚያ ድርጅት ዝቅ ብሎ በቀድሞው ኖሬላ ግቢ ውስጥ በሚገኘው ዋና መ/ቤት የግዥ ክፍል  የዋስትና ማስከበሪያ ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) በሲ.ፒ፣ኦ በመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት (Defence Construction Design Enterprise) ስም በማዘጋጀት ከዋና እና ኮፒ ዋጋ ማቅረቢያ ጋር ለየብቻ በሰም በታሸገ ኢንቬሎፕ በማቅረብ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ጨረታው በአስረኛው ቀን ከቀኑ 08፡00 ሠዓት ተዘግቶ ከቀኑ 08፡30 የድርጅቱ ህጋዊ ወኪሎች ባሉበት ይከፈታል፡፡

ዕእለቱ ቅዳሜና  እሁድ ወይም የበአላት ቀን ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ከቀኑ 08፡00 ሠዓት ተዘግቶ ከቀኑ 08፡30 ሠዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡

ተ.ቁ የተሸከርካሪው አይነት የአንድ ቀን ዋጋ ማብራሪያ ካለ
ነዳጅ ከአከራይ ሲሆን ነዳጅ ከተከራይ ሲሆን
1 ከ12-15 መቀመጫ ወንበር ያለው (ሰርቪስና ለሌሎች የሙሉ ቀን ስራዎች)      
2 ከ15-24 መቀመጫ ወንበር ያለው (ጠዋትና ማታ ለሰርቪስ ስራ)      

ማስታወሻ፡- የቀረበው ዋጋ ቫትን ማካተቱና አለማካተቱ መጠቀስ ይኖርበታል፡፡

  • ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
  • አዲስ አበባ ወሎ ሰፈር አምባሰል ህንጻ ፊት ለፊት ብራና ማተሚያ ድርጅት ዝቅ ብሎ በቀድሞው ኖሬላ ግቢ ውስጥ
  • የስልክ ቁጥር፡- 0118960629/ 0118960632