ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ. የካሣ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን ቀላልና ከባድ የተጐዱ ተሽከርካሪዎችንና ልዩ ልዩ የተሽከርካሪ አካላት ቅሪቶችን እንዲሁም የድርጅቱን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Vehicle Sale
- Phone Number : 0115549650
- Source : Reporter
- Posted Date : 05/09/2022
- Closing Date : 05/21/2022
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ
Ethio Life and General Insurance S.C
ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ. የካሣ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን ቀላልና ከባድ የተጐዱ ተሽከርካሪዎችንና ልዩ ልዩ የተሽከርካሪ አካላት ቅሪቶችን እንዲሁም የድርጅቱን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
- ተሽከርካሪዎችን ለመግዛት በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ሁሉ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ከቼራሊያ ዝቅ ብሎ በሸዋ ዳቦ 350 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው የኩባንያው ተሽከርካሪዎች ማቆያ (Recovery Site) ከግንቦት 1 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ግንቦት 12 ቀን 2014 ዓ.ም ባሉት የሥራ ቀናት በማምጣት ማየት ይቻላል፡፡
- ተጫራ(ች ተሽከርካሪዎችን የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎኘ ከሰኞ ግንቦት 1 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ግንቦት 12 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ከመስቀል ፍላወር ወደ ደንበል በሚወስደው መንገድ ቱሊፒ ሆቴል ፊት ለፊት 5ኛ ፎቅ በሚገኘው የኩባንያው ዋና መ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይቻላል፡፡
- ተጫራ(ች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 10% በባንክ በተረጋገጠ ማዘዣ ለጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው አሸናፊዎች የተሽከርካሪውን ዋጋ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ የጨረታ ውጤት በተገለፀ በ5 ቀናት ውስጥ ከፍለው በ10 ቀናት ውስጥ ንብረቱን ከግቢው ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ዋጋ ተንተርሶ ሌላ ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡ የጨረታ ዋጋ አባዝቶ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ተሽከርካሪው በጨረታ እስከተሸጠበት ድረስ የሚፈለግ ግብርና ታክስ ቢኖር ጨረታውን አሸንፈው የሚገዙ አይጠየቁበትም፡፡ ተሽከርካሪው ከተሸጠ በኋላ የሚፈለግ ግብር ታክስና እንዲሁም የቦሎ ክፍያና ተያያዥ ቢኖር የገዥው ኃላፊነት ይሆናል፡፡
- ተጫራ(ች የሚያቀርቡት ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን የሚያጠቃልል መሆኑን በግልፅ ሁኔታ በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ካልተገለፀ በስተቀር ባቀረቡት ዋጋ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ተጨምሮ የሚታሰብ ይሆናል፡፡
- አሸናፊ ተጫራ(ች ተሽከርካሪውን በራሳቸው ወጪ አስነስተው ይወስዳሉ፡፡
- ተጫራ(ች ስለተሽከርካሪዎቹ መንገድ ትራንስፖርት በሰጠው ውሳኔና በጨረታው ሰነድ ላይ በተገለፀው መሠረት ከግምት ውስጥ በማስገባት ዋጋ መስጠት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ግንቦት 13 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ኩባንያው ዋና መ/ቤት ይከፈታል፡፡ ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115549650/0911157195/0911153169 ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡