ፀሐይ ባንክ አ.ማ ከዚህ በታች በተገለጹት የሥራ መደቦች የሰው ኃይል በማቅረብ ሙያዊ ፍቃድ ያላቸው ድርጅቶችን በማወዳደር አገልግሎት መግዛት ይፈልጋል፡፡

Tsehay-Bank-logo

Overview

 • Category : Purchases
 • Posted Date : 05/09/2022
 • Phone Number : 0114705055
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 05/31/2022

Description

የሰው ኃይል አቅርቦት የአገልግሎት ግዥ

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ፀባ/006/2014

ባንካችን ከዚህ በታች በተገለጹት የሥራ መደቦች የሰው ኃይል በማቅረብ ሙያዊ ፍቃድ ያላቸው ድርጅቶችን በማወዳደር አገልግሎት መግዛት ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ የሥራው/የአገልግሎቱ  ዓይነት
1 ጥበቃ
2 የገንዘብ አጃቢ (ጥበቃ)
3 መልዕክት ሰራተኛ
4 ጽዳት /ከነጽዳት ዕቃዎች አቅርቦት ጋር/
5 ጽዳትና መልዕክት ሰራተኛ
6 ሾፌር(የመኪና አሽከርካሪ)
7 ሾፌር መካኒክ (የመኪና)
8 ሞተረኛ
9 መኪና አጣቢ
10 የጉልበት ሰራተኛ

 ስለሆነም በጨረታው የሚወዳደሩ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፤

 1. ከሠራተኛና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ለ2014 ዓ.ም የታደሰ የቅጥር ሥራ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው ፡፡
 2. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዶቹ ጋር የታደሰ የንግድ ፈቃድ ቅጅ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የቲን የምስክር ወረቀት እና ከገቢዎች ሚኒስቴር ከግብር ነፃ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 3. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከግንቦት 02 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት የሥራ ቀኖች ማለትም ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 11:00  ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ  2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት የማይመለስ መቶ ብር /100.00/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
 4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስታ እስከ ግንቦት 23 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ በዋና መ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 9፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባንኩ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
 5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ /Bid Bond/ ብር 25‚000.00 ቢያንስ ለ90 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ በባንክ በተመሰከረለት የባንክ ዋስትና ወይም ሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የጨረታው መዝጊያ ሰዓት ካለፈ በኋላ የሚመጣ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
 6. ተጫራቾች በሥራው/ዘርፉ/ ለ3 ዓመታትና ከዚያ በላይ የቆዩ መሆን አለባቸው፤ ከሶስት ዓመት በታች ልምድ ያለው ድርጅት ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
 7. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ

 • በስልክ ቁጥር +251 11 4 70 50 55 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡ በአካል በመቅረብ መረጃ ማግኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች ግሎባል ሆቴል ፊት ለፊት ፣ ባላገሩ ህንፃ 5ኛ ፎቅ  የባንኩ ፋሲሊቲስ ማኔጅመንት መምሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ፀሐይ ባንክ አ.ማ

ስልክ +251 11 4 70 50 55/+251 11 4 70 56 13

አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ