የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማህበር እ.ኤ.አ የሁለት ዓመት የማህበሩን ሂሳብ በዉጭ የሂሳብ ኦዲተር (External Auditor) አወዳድሮ ማስመርመር ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Auditing Related
 • Posted Date : 05/11/2022
 • Phone Number : 0115519120
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 05/21/2022

Description

የኦዲት ጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማህበር እ.ኤ.አ ( ከጁላይ 2019 ጀምሮ እስከ ጁን 2021) ያለዉን የሁለት ዓመት የማህበሩን ሂሳብ በዉጭ የሂሳብ ኦዲተር (External Auditor) አወዳድሮ ማስመርመር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ማንኛዉም ከዚህ በታች የተገለጸዉን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች ድርጅቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

 1. የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለዉ፣
 2. የታደሰ የሙያ ማረጋገጫ ፈቃድ እና የተፈቀደላቸዉ ኦዲተር ስለመሆናቸዉ ማረጋገጫ ያላቸዉ
 3. የተመዘገበ የቫት ሰርትፊኬት
 4. የወቅቱን ግብር የከፈለና ክሊራንስ ማቅረብ የምትችሉ
 5. ዝርዝር የድርጅታችሁን አደረጃጀት
 6. ዝርዝር እቅዳችሁን፣ የኦዲት አገልግሎት ሥራዉን የምታከናዉኑበን ዋጋ እና ሥራዉን አጠናቆ የኦዲት ሪፖርን ለማቅረብ የሚያስፈልገዉ ጊዜ የሚገልጽ ሰነድ
 7. በሂሳብ ምርመራ በቂ ሙያና የስራ ልምድ ያላችሁ (በሰራችሁበት ተቋማት እስከ አምስት ያሉትን ማስረጃ መቅረብ የሚችል)
 8. የዋጋ ማስከበሪያ ሲፒዮ 3,000 ብር ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 9. ተወዳዳሪዎች የቴክኒካል እና ፍይናንሻል ማስረጃችሁን ለይታችሁ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማህተም አረጋግጣችሁ ማስገባት ይጠበቅባችኋል፡፡
 10. ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
 • ስለሆነም ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ ቀናት ዉስጥ በስራ ሰዓት ቅዳሜን ጨምሮ ለገሃር በሚገኘዉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማህበር ጽ/ቤት በመቅረብ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
 • ለተጨማሪ ማብራሪያ ፡ -ስልክ ቁጥር ፤- 0115519120 ወይም 8679