አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውንና በሠንጠረዡ የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረት ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Abissiniya-Bank

Overview

  • Category : House & Building Foreclosure
  • Phone Number : 0115546737
  • Source : Reporter
  • Posted Date : 05/11/2022
  • Closing Date : 06/10/2022

Description

      ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውንና በሠንጠረዡ የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረት ባሉበት  ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡

  • ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋውን ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ፡፡
  • የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት/ንብረቶች መረከብ ይኖርበታል፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል፡፡
  • ተበዳሪው/መያዣ ሰጪው በሐራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል፡፡
  • የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን ፣ግብር፤በተተቀሱት ንብረቶች ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ 15% ቫት እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጪዎች ገዢ ይከፍላል፡፡ውዝፍ የሊዝ ዕዳ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ቀሪ የወደፊት የሊዝ ክፍያ ዕዳ ወደ አሸናፊው /ገዢ የሚተላለፍ ይሆናል፡፡
  • ንብረቱን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አሲዞ ለመጎብኘት ወይም ለማየት ይቻላል፡፡
  • በባንኩ ብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟሉ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢዎች ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል፡፡
  • የጨረታው ቦታ ንብረቱ በሚገኝበት ጎንደር ከተማ ነው፡፡
  • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115 54 67 37 / 0115 150711 አ.አ በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
  • ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 

.

የተበዳሪው ስም ከተበዳሪው የሚፈለግበት

ቀሪ ዕዳ

የመያዣው ሰጪው ስምየንብረቱ ዓይነትና አገልግሎትየቦታው ስፋትየባለቤት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻየጨረታ መነሻ ዋጋ ጨረታው የሚካሄድበት ቀን  

የምዝገባ

ሰዓት

የጨረታ

ሰዓት

 

1

አቶ አለማየሁ ማሞእስከ ጥር 07 ቀን 2012ዓ.ም ድረስ  ብር 23,214,865.39ተበዳሪውመኖሪያ ቤት261ካ.ሜK015/02-6-89-337-7626/02አ/አ lከተማ ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 1412,347.000.00ሰኔ 3   ቀን 2014 ዓ.ም 4:30-5:30 5:30-6:00