የኢትዮጵያ ሴቶች ፌደሬሽን በሲቪል ማህበራት አዋጅ አሰራር መሰረት በስሩ ያሉትን ተቋማትና የራሱን ከ2014-2016 ሂሳብ ህጋዊ እውቅና ባለው ኦዲተር ማስመርመር ይፈልጋል፡፡

Ethiopian-Womens-Federation-logo-1

Overview

 • Category : Auditing Related
 • Posted Date : 05/15/2022
 • Closing Date : 05/27/2022
 • Phone Number : 0115573454
 • Source : Reporter

Description

የኦዲተር አገልግሎት ግልፅ ጨረታ

የኢትዮጵያ ሴቶች ፌደሬሽን በሀገሪቱ ውስጥ ከ50 በላይ የሴት ማህበራትና ከ8 ሚሊዮን በላይ ሴቶችን በስሩ አቅፎ የያዘ አገር በቀል የሲቪክ ፌደሬሽን ሲሆን ሴቶች እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑና ያሉባቸውን ዘርፈ ብዙ ኢኪኖሚያዊ፣ማህበራዊና ፖለቲካዊ ችግሮች በተደራጀና በተቀናጀ መንገድ ለመፍታት የተቋቋመ ሲቪክ አደረጃጃት ነው፡፡

ፌደሬሽኑ በሲቪል ማህበራት አዋጅ አሰራር መሰረት በስሩ ያሉትን ተቋማትና የራሱን ከ2014-2016 ሂሳብ ህጋዊ እውቅና ባለው ኦዲተር ማስመርመር ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በዚህ ጨረታ መወዳደር የምትፈልጉ ማናቸውም ህጋዊ ተጫራቾች አዲስ አበባ ቦሌ ወሎ ሰፈር ከሸዋ ሱፐር ማርኬት ፊት ለፊት አልታ ኮምፒውተር ያለበት ህንፃ ግራውንድ ላይ በመምጣት ዝርዝር መረጃ ማግኘት የምትችሉ ሲሆን የምትጫረቱበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ እንድታቀርቡ እያሳሰብን ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10/አስር/ የስራ ቀናት ሲሆን ከ11ኛው ቀን ጀምሮ የመጀመሪያው የስራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ 4፡00 ተዘግቶ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ለጨረታው ሲቀርቡ ማሟላት የሚጠበቅባቸው ሰነዶች፡-

 1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ
 2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት
 3. የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት
 4. የኦዲት ቦርድ ፈቃድ ሰርተፍኬት
 5. የተጨማሪ ታክስ ግብር ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት
 6. የጨረታ ማስከበሪያ ያስገባችሁበትን ዋጋ 5% ሲ.ፒ.ኦ

መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ፡- የፋይናንስ ስልክ ቁጥር 0115 57 34 54