በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 የሚገኘው ፋና ቦሌ ሸ/ኃ/የተ/የህ/ሥራ ማህበር የ17/17 ህብረተሰብ ልማት ማዕከል ደረጃቸው 7 (ሰባት) እና ከዚያ በላይ የሆኑትን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የአዳራሽ የብፌ ቤት እና የበረንዳ ኮርንስ በጅብሰን ቦርድ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Construction Service & Maintenance
 • Posted Date : 05/15/2022
 • Phone Number : 0116184076
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 05/27/2022

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 የሚገኘው ፋና ቦሌ ሸ/ኃ/የተ/የህ/ሥራ ማህበር የ17/17 ህብረተሰብ ልማት ማዕከል ደረጃቸው 7 (ሰባት) እና ከዚያ በላይ የሆኑትን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የአዳራሽ የብፌ ቤት እና የበረንዳ ኮርንስ በጅብሰን ቦርድ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ፡-

 • ሎት አንድ
 1. የአዳራሽ፣ የብፌ ቤት እና የበረንዳ ኮርኒስ እና ኮለን ሥራ
 2. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሠ ህጋዊ የንግድ የሥራ ፈቃድ፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት ወቅታዊ የግብር ክፍያ ማረጋገጫ፣ የቫት/የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ፣ በአቅራቢዎች ስም ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው ወረቀትና ሌሎች ሠነዶችን አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
 3. ተጫራቾች አሻሚና ግልፅ ባልሆነ ሁኔታ የጨረታ ዋጋ በመሙላት መወዳደር (ለመወዳደር መሞከር) ከጨረታ ውጭ ያደርጋል፣
 4. ሠነድ ሊወስዱ ሲመጡ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሠነድ መግዛት ይኖርባቸዋል፣
 5. ተጫራቾች የፋይናሻል ጨረታ ሠነድ ተሞልቶ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በተለያየ ፖስታ ታሽጎ ኦርጅናል እና ኮፒ ተብሎ ተፅፎበት በሁለቱም ፖስታዎች ላይ አድራሻና የፕሮጀክቱን ስም በመፃፍ ህጋዊ ማህተም በማሳረፍ እና በመፈረም ታሽጎ አንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም የቴክኒካል ሠነዱ ተሞልቶ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በተለያየ ፖስታ ታሽጎ ኦርጅናል እና ኮፒ ተብሎ ተፅፎበት በሁለቱም ፖስታዎች ላይ አድራሻን በመፃፍ ህጋዊ ማህተም በማሳረፍ እና በመፈረም ታሽጎ አንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 6. ተጫራቾች የጠቅላላ ዋጋ የጨረታውን 2% በሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣
 7. ጨረታው በወጣበት በአስረኛው ቀን ከጧቱ ከ4፡00 ሰዓት ላይ የጨረታውን ሣጥን ይዘጋና በዕለቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልፅ የ17/17 ህብረተሰብ ልማት ማዕከል ይከፈታል፡፡ መያያዝ ያለበት ከቴክኒካል ሠነድ ኦርጅናል ጋር ወይም ለብቻው በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታው ሠነድ ስርዝ ድልዝ ወይንም የድምር ስህተት መኖር የለበትም፡፡ ይህ ከሆነ ተጫራቾች ያስገቡት ሠነድ ውድቅ ይሆናል፣ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታ ሣጥን መክፈቻ ሥነ-ሥርዓትን አያስተጓጉልም፡፡
 8. ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀን አየር ላይ የሚውል ሲሆን ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፣
 9. የጨረታው ሣጥን ከታሸገና ሠነዶቹ መከፈት ከተጀመረ በኋላ የሚመጣ ማንኛውም ተጫራቾች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡ የጨረታውን መመሪያ አለማክበር ከጨረታው ያሰርዛል፣
 10. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ድርጅት የቅድመ ክፍያ፣ የመልካም ሥራ አፈፃፀም፣ የውል ማስከበሪያ ዋስትና በማስያዝ ውል መግባት አለበት፡፡
 11. ከሥራው ከሚጠበቀው ከፍተኛ ጥራትን የማስጠበቅ ግብና በበጀት መሠረት ሥራውን የመፈፀም ግዴታን መሠረት አድርጎ ማዕከሉ ካስጠናው የመሐንዲስ ግምት (10%) አስር በመቶ በላይ እና በታች የተመዘገቡ የጠቅላላ ዋጋ ውጤቶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡ ዝቅተኛ የዋጋ መጠን ያስመዘገበው ተጫራች ከዚህ ወሰን ውጭ ከሆነ፣ የሚቀጥለው በወሰኑ ውስጥ ያለ ዝቅተኛ ዋጋ አቅራቢ ተጫራች አሸናፊ ይሆናል፡፡
 12. የ17/17 ህብረተሰብ ልማት ማዕከል ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
 13. ተጫራቾች የሚሰራውን ሥራ ቦታው ድረስ በመገኘት መመልከት ይኖርባችኋል፡፡

አድራሻ፡– የፋና ቦሌ ሸ/ኃ/የተ/የህ/ሥራ ማህበር 17/17 ህብረተሰብ ልማት ማዕከል ቅጥር ግቢ ውስጥ የማዕከሉ ፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቀርበው ሠነዱን መግዛት ይቻላል፡፡

ለበለጠ መረጃ

(0116184076        0116187529      0116186504     0116624761