ይርጋጨፌ ቡና ገበሬዎች ኃላ/የተ/የኅብረት ሁለገብ ህንጻና የገበያ ማዕከል ግንባታ ፕሮጀክት የአዋጭነት ጥናት በማሰራት ለፋይናስ ተቋማት ማቅረብ ይፈልጋል፡፡

Yirgacheffe-Coffee-Farmers-Cooperative-logo

Overview

 • Category : Construction Service & Maintenance
 • Posted Date : 05/15/2022
 • E-mail : yirgacheffe@ethionet.et 
 • Phone Number : 0114717019
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 05/30/2022

Description

ቁጥር YCFCU/20486/14

  ቀን 04/09/2014

የአማካሪ ድርጅት የጨረታ ማስታወቂያ

የይርጋጨፌ ቡና ገበሬዎች ኃላ/የተ/የኅብረት ሥራ ዩንየን ቡና ከአባል ማህበራት አርሶ አደርች ቡና በመሰብሰብ እና በማከማቸት ጥራቱንና ደረጃውን የጠበቀ ቡና በማዘጋጀት ወደ ውጭ ሀገር በመላክ የተሰማራ ድርጅት ነው ፡፡

በመሆኑም ቡና ተቆልቶና ተፈጭቶ ጥራቱንና ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ ለውጭ ሀገር ለመላክ የማስፋፍያ ፕሮጀክት እና በዲላ ከተማ ለሚያስገነባው ሁለገብ ህንጻና የገበያ ማዕከል ግንባታ ፕሮጀክት  የአዋጭነት ጥናት በማሰራት ለፋይናስ ተቋማት ማቅረብ  ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በዘርፉ የተሰማራችሁ ህጋዊ ድርጅቶች  አወዳድሮ የአዋጭነት ጥናት ማሰራት ይፈልጋል በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ  ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ዉስጥ የጨረታ ሰነድ በዩንየኑ የሰዉ ኃይልና ንብረት አስተዳደር ክፍል በአካል ቀርባቹ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

 1. የዘመኑ ታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለዉ ድርጅት እና የዘመኑን የግብር የከፈሉበት ክሊራንስ መረጃ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ እና የቲን ምዝገባ ሰርቲፊኬት ማሰረጃ ማቅረብ የሚችል፣
 2. የቢዝነስ ማመከር እና የአዋጭነት ጥናት ላይ በቂ ልምድና ክህሎት እንዲሁም ፕሮፊሽናል ፍቃድ ያለው፣
 3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ በየኒየኑ የሰ/ሀ/ን/አስተ/ክፍል ድረስ በመምጣት የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ 100.00 ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፤
 4. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) በይርጋጨፌ ቡና ገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን ስም 10,000.00 (አስር ሺህ) ብር በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
 5. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው የቴክኒካል እና የፋይናንሻል ሰነድ በተለያየ ኤንቨሎፕ ሆኖ አንድ አንድ ኦርጂናል እና ሁለት ሁለት ኮፒዎችን በማድረግ ማስታወቂያዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስር (10) ተከታታይ የስራ ቀናት ዉስጥ ከዚህ በታች በተገለፀዉ በድርጅቱ አድራሻ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
 6. ጨረታው በቀን 22/09/2014 ከጥዋቱ 4.30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 5፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዩኒየኑ ጽ/ቤት ውስጥ በግልጽ ይከፈታል፡፡
 7. ለጨረታዉ የተያዘዉ ዋስትና ለተሸናፊዎቹ የጨረታዉ ዉጤት ሲገለፅ የሚመለስ ሲሆን በአሸናፊዎች የዉል ግዴታ ፈፅመዉ የዉሉ ማስከበሪያ ዋስትና ሲያሲዙ ይመለሳል፡፡
 8. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡

አድራሻ፡-

ቃሊቲ አደባባይ ወደ ሃና ማርያም በሚወስደዉ   በኦሮሚያ ዉሃ ሥራዎች ጎን   

  ስልክ፡-011 471 70 19/18/17 

Physical Address:

Akaki kalit Sub city Around Kality Square Behind CCRDA,

Next to Oromia Water Works Construction Bruea, on the road of Hana Maryam in

Yergacheffe Coffee Farmers Cooperative Union Ltd

E-mail  yirgacheffe@ethionet.et  P.O.BOX: 122641

TEL:+251(0)114-71-70-19/18/17 FAX: +251(0)114-71-70-10