አቢሲንያ ባንክ አ.ማ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውንና በሰንጠረዡ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እንደተሻሻለው ለባንኮች በተሰጠው ስልጣን መሠረት ንበረቶቹ በሚገኙበት ቦታና ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ እወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : House & Building Foreclosure
- Posted Date : 05/15/2022
- Closing Date : 06/16/2022
- Phone Number : 0462121710
- Source : Reporter
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
አቢሲንያ ባንክ አ.ማ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውንና በሰንጠረዡ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እንደተሻሻለው ለባንኮች በተሰጠው ስልጣን መሠረት ንበረቶቹ በሚገኙበት ቦታና ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ እወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ተጫራቾች ለጨረታው ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋውን ¼(አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ አ.ማ ስም ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ. ይመለስላቸዋል፡፡
- ተበዳሪው/ መያዣ ሰጪው በሐራጁ ቀንና ሰዓት ጨረታ በሚካሄድበት ቦታ መገኘት ይችላሉ፡፡ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል፡፡
- ጨረታው የሚካሄደው ንብረቶቹ በሚገኙበት በኦሮሚያ ብ/ክ/መ፣ ዱከም ከተማ ጠድቻ (01) ቀበሌ ነው፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን፣እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጪዎችን ገዥ ይከፍላል፡፡ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ቀሪ የወደፊት የሊዝ ክፍያ እዳ ወደ አሸናፊው/ገዥው የሚተላለፍ ይሆናል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ንብረቱ በሚገኝበት የከተማ አስተዳደር ዘንድ ቀርቦ ባሸነፈበት ንብረት ላይ የሚከፈሉ ክፍያዎችን፣ ግብር እና ታክስ ይከፍላል፡፡
- የጨረታው አሸናፊዎች/ገዥ ለመንግስት የሚከፈል 15% (አስራ አምስት በመቶ) የተጨማሪ እሴት ታክስ ካለ ይከፍላሉ፡፡
- ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ ለመጎብኘት የሚቻል ሲሆን፣ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች 046-212-1710 እና በ046-212-2346 ሀዋሳ በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
- በባንኩ የብድር ፖሊሲና መመሪያ መሠረት የብድር መስፈርት ለሚያሟሉ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢዎች ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል፡፡
- ንብረቶቹ የሚገኙበትን ሁኔታ ዘውትር በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ወይም ማየት ይቻላል፡፡
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
ተ.ቁ | የተበዳሪው ስም | ከተበዳሪው የሚፈለግበት ቀሪ ዋና ዕዳ | የመያዣ ሰጪው ስም | ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ | የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር | ጨረታው የሚካሄድበት ቀንና ዓ.ም | የምዝገባ ሰዓት | የጨረታ ሰዓት | ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ
| የንብረቱ አገልግሎት | የቦታው ስፋት (በካ.ሜ) | የባለቤትነት ማረጋገጫ/ካርታ ቁጥር | ጨረታው የወጣበት ጊዜ |
1 | አቶ እየብ ወንድወሰን ወጋየሁ | እስከ ሚያዘያ 26 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ብር 2,556,544.80 | ተበዳሪው | ኦሮሚያ ብ/ክ/መ፣ ዱከም ከተማ፣ ጠድቻ (01) ቀበሌ | 2,486,122.21 | ሰኔ 08 ቀን 2014 ዓ.ም
| 4፡30-5፡30 | 5፡30-6፡00 | ንብረቱ በሚገኝበት ኦሮሚያ ብ/ክ/መ፣ ዱከም ከተማ፣ ጠድቻ (01) ቀበሌ | ለመኖሪያ | 200.00 | BMD-83691/3681/01/G-01-575/”00″ |
ለሁለተኛ |
2 | አቶ ይታገሱ ደበበ ገብረሚካኤል | እስከ ሚያዘያ 26 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ብር 1,732,193.66 | ተበዳሪው | ኦሮሚያ ብ/ክ/መ፣ ዱከም ከተማ፣ ጠድቻ (01) ቀበሌ | 1,503,219.70 | ሰኔ 09 ቀን 2014 .ም
| 4፡30-5፡30 | 5፡30-6፡00 | ንብረቱ በሚገኝበት ኦሮሚያ ብ/ክ/መ፣ ዱከም ከተማ፣ ጠድቻ (01) ቀበሌ | ለመኖሪያ | 140.00 | BMD-5221/109/01/G-01-576/”00″ |
ለሁለተኛ |