ሕብረት ባንክ አ.ማ. በአለም ገና ቅርንጫፉ በኩል ለሰጠዉ ብድር በመያዣነት የያዛቸዉን ከዚህ በታች የተመለከቱትን የባንክ አክሲዮኖች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/1992 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልጽ ሐራጅ (ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡
Overview
- Category : Other Foreclosure
- Posted Date : 05/14/2022
- Closing Date : 05/31/2022
- Phone Number : 0113662022
- Source : Reporter
Description
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ፤
ሕብረት ባንክ አ.ማ. በአለም ገና ቅርንጫፉ በኩል ለሰጠዉ ብድር በመያዣነት የያዛቸዉን ከዚህ በታች የተመለከቱትን የባንክ አክሲዮኖች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/1992 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልጽ ሐራጅ (ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡
የቅርንጫፍ ስም | የተበዳሪ ስም | የንብረት አስያዦች ስም | አክሲዮኖቹ የሚገኙበት ድርጅት (አ.ማ.) | የሰርተፊኬት ቁጥር | የአክሲዮን ብዛት | የአንዱ አክሲዮን ዋጋ /በብር/ | የሐራጅ መነሻ ዋጋ /በብር/ | ሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት |
አለም ገና | አቶ ቢኒያም በየነ አብርሃ | አቶ ቢኒያም በየነ አብርሃ | አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ | AAG 07188 | 116,594 | 25 (ሃያ አምስት) ብር | 25 (ሃያ አምስት) ብር | ግንቦት 23 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት |
AAI 07188 | 20,000 | 25 (ሃያ አምስት) ብር | 25 (ሃያ አምስት) ብር |
የሐራጅ ደንቦች
- ተጫራቾች መጫረት የሚፈልጉትን የአክሲዮን ብዛት በ100 (አንድ መቶ) አባዝተው የሚገኘው መጠን ላይ አንድ አራተኛ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊ የሆነዉ ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአስራ አምስት (15) ቀናት ዉስጥ አጠቃልሎ ካልከፈለ ያስያዘዉ ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሀራጅ ሲቀርብ ለሚታየዉ የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡
- በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪዎች እና አስያዦች ብቻ ናቸዉ፡፡
- የሐራጅ ሽያጩ የሚካሄደዉ አዲስ አበባ ንግድ ሥራ ኮሌጅ ፊትለፊት በሚገኘው የባንኩ አዲሱ ዋና መሥሪያ ቤት፣ 26ኛ ፎቅ ባለዉ የሕግ መምሪያ አዳራሽ ዉስጥ ነዉ፡፡
- የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል፡፡ በሐራጁ ሰላሳ (30) ደቂቃዎች የተጫራች ምዝገባ አይካሄድም፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸዉ በህግ የተወሰኑ የታክስና ግብር የስም ማዛወሪያ ጭምር /የጨረታዉ አሸናፊ/ገዥዉ ይከፍላል፡፡
- ባንኩ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚቀርቡ ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- አንድ ተጫራች ከላይ በሰንጠረዡ የተገለጸው የአክሲዮን ብዛት በሙሉም ሆነ በከፊል ለመግዛት መጫረት ይችላል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚሆነው ለአንድ አክሲዮን በሚቀርበው ከፍተኛ ዋጋ መሰረት ከከፍተኛው ወደ ዝቅተኛ በቀረበው ዋጋ ቅደም ተከተል ነው፡፡
- አግባብነት ያላቸው በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የወጡ መመሪያዎች ሁሉ ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0113662022 አለም ገና ቅርንጫፍ ወይም 0114-70 03 15/69/47 ሕግ አገልግሎት መምሪያ ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡