ቢ ዲ አር ኤም ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል/ማህበር በአዲስ አበባ፡ ኢትዮጵያ የሚገኘውን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር (UNHCR) በመወከል ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች፣ ያገለገሉ ጀነሬተሮች፣ ያገለገለ ፈርኒቸር፣ ያገለገሉ የአይ ሲ ቲ እቃዎች፣ ግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Vehicle Sale
 • Posted Date : 05/21/2022
 • Phone Number : 0945555550
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 06/10/2022

Description

የUNHCR (የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር) ያገለገሉ ተሸርካሪዎችና እቃዎች ግልፅ ጨረታ

ቢ ዲ አር ኤም ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል/ማህበር በአዲስ አበባ፡ ኢትዮጵያ የሚገኘውን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች  ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር  (UNHCR)  በመወከል  ባለቤትነታቸው የተባበሩት  መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር የተባበሩት መንግስታት የዓለም የምግብ  ፕሮግራም (WFP)  እና የተባበሩት መንግስታት የህዝብ  ገንዘብ  ፈንድ (UNFPA)  የሆኑ  ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች፣ ያገለገሉ ጀነሬተሮች፣  ያገለገለ  ፈርኒቸር፣  ያገለገሉ የአይ ሲ ቲ እቃዎች፣ ያገለገሉና ከጥቅም  ውጭ  የሆኑ መለዋውጫዎችና የውሀ ፓምፖች እንዲሁም የተለያዩ እቃዎችን ለመሸጥ ግንቦት 27 ቀን 2014 ዓ/ም 5:00 ላይ ግልፅ ጨረታ ያካይዳል።

የተሽከርካሪዎቹ ማየት የሚፈልጉ ተጫራቶች ከሰኞ ግንቦት 15 2014 እስከ አርብ ግንቦት 26 ቀን 2014 ዓ/ ም ከጠዋቱ 3:00 እስከ 10:00 ኮተቤ 02 ቀበሌ ጎል ኢትዮጵያ አጠገብ በሚገኘው መጋዘን መመልከት ይችላሉ:: ሲሆን የእቃዎቹ ሁኔታች ማየት የሚፍልጉ ጅጅጋ ከተማ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር (UNHCR) መጋዘን በመሄድ ስለ እቃዎቹ ሁኔታና አይነት መመልከት ይችላሉ።

የተሳታፊዎች ምዝገባና ሲፒኦ ማስያዝ ከሰኞ ግንቦት 15 2014 እስከ አርብ ግንቦት 26 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ ከጠዋቱ 3:00 እስከ 10:00 ኮተቤ 02 ቀበሌ ጎል ኢትዮጵያ አጠገብ በሚገኘው መጋዘን ይከናወናል። በጨረታው ቀን መመዝገብ ይሁን ሲፒኦ ማስያዝ አይቻልም። ለመጫረት  ፍላጎት  ያለው  ማንኛውም  ግለሰብ  ይሁን ድርጅት ብር  500  በመክፈል  መመዝገብና ለሚጫረትባቸው ለእያንዳንዱ የመኪና የጨረታ መደብ ብር 300,000 (ሶስት  መቶ ሺ ብር)  ለእያንዳንዱ የእቃዎች የጨረታ መደብ ብር 150,000 (መቶ ሀምሳ ሺ ብር) ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (ሲ ፒ ኦ) በቢ ዲ አር  ኤም ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግል/ማህበር ስም እስከ አርብ ግንቦት 26 ቀን 2014 ዓ/ም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

አሸናፊዎች ለአሸነፉት ተሽከርካሪ ይሁን ሌሎች የጨረታ መደብ ሙሉውን ክፍያ ጨረታው ከተካሄደበት ቀን አንስቶ ባሉ ቀጣይ አምስት የስራ ቀናት ውስጥ ማለት እስከ አርብ ሰኔ 3 ቀን 2014 ዓ/ም 11፡00 ሰአት ሙሉን ክፊያውን በቢ ዲ አር  ኤም ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር በዳሽን ባንክ በሚገኘው ሂሳብ ቁጥር 5254001764064  ቀሪውን  ገንዘብ  መክፈል ይኖርባቸዋል። ከፊል ክፍያዎች  ተቀባይነት የላቸውም። በተቀመጠው ጊዜ ገደብ መክፈል ያልቻሉ ተጫራቶች  ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ  ያጣሉ። ድርጅቱ ሌሎች አማራጮችን የመውሰድ መብቱ የተጠበቅ ነው።

ቢ ዲ አር  ኤም ትሬድንግ ኃ/የተ/የግል/ማህበር  ለተሸጡ ተሽከርካሪዎች ይሁን እቃዎች ምንም አይነትሃላፊነት አይወስድም። ገዢዎች ለገዙዋቸው መኪኖችን አስፈላጊ ሰነዶችን ከተረከቡ ብኃላ በ15 ቀናት ውስጥ  አስፈላጊው የግብር የታክስ የቀረጥ  ግዴታዎች እና ተያያዥ ወጪዎች  ከፍለው በስማቸው አዘዋውሮ መውሰድ ይኖርባቸዋል። ይህ  ሳይሆን ሲቀር የከፈሉት ገንዝብ ለድርጅቱ ገቢ ተደርጎ መኪኖችን በቀጣይ ጨረታ ይወጣሉ::

አሸናፊዎች የገዙት ተሽከርካሪ መረከብ የሚችሉ በኢትዮጵያ መንግስት ህግና ደንብ መሠረት ለመንግስት መከፈል ያለባቸው የግብር የታክስ የቀረጥ  ግዴታዎችና ተያያዥ የስም ማዘዋወሪያ  ወጪዎች  እና በኢትዮጵያ መንግስት የሚፈለገውን አስፈላጊ ሰነዶችን እና የወረቀት ስራዎችን  ካጠናቀቁ በኋላ ብቻ ነው።

አሸናፊዎች የገዙዋቸው ተሽከርካሪዎች ወይም እቃዎች በተቀመጠው ጊዜ ገደብ ማንሳት ይኖርባቸዋል። በወቅቱ የማያነሱ አሸናፊዎች የማቆያ ክራይ በቀን 500 ብር ይከፍላሉ።

 • ተጫራቾች ለሚገዙዋቸው ተሽከርካሪዎች  እና እቃዎ  ሲወስዱ  የግል  መጓጓዣ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
 • በኢትዮጵያ መንግስት የሚከፈልን ማንኛውም ግብር ቀርጥ የሽያጭ ወይም የስም ዝውውር ክፍያእና ሌሎች።
 • ክፍያዎች የገዢው ኃላፊነት ነው። እነዚህ ወጪዎች ከሽያጭ ዋጋ የማይቀነሱ ይሆናል።
 • ሁሉም ተሸከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ እንዲሁም በማይመለስ መልኩ ይሸጣሉ።
 • ድርጅቱ ከላይ የተቀመጡት መስፈርቶች ሳያሟሉ ወይም ለቀረበው የጨረታ መደብ ተመጣጣኝ ዋጋ አልተሰጠም ብሎ ካመነ ከተጫራቶች የተሰጠው ዋጋ ውድቅ የማድረግ መብቱ የተጠበቀ ነው።
 • መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
 • ለበለጠ መረጃ 0945555550 ወይም 0907767777 ይደውሉ