ብርሃን ባንክ አ.ማ ከዚህ በታች በዝርዝር የተገለጸዉን ቢሾፍቱ ከተማ የሚገኝ መኖሪያ ቤት ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Berhan-International-Bank-S.c-logo-3

Overview

 • Category : House & Building Sale
 • Posted Date : 05/21/2022
 • Phone Number : 0116182624
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 06/14/2022

Description

የመኖሪያ ቤት ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

ብርሃን ባንክ አ.ማ ከዚህ በታች በዝርዝር የተገለጸዉን ቢሾፍቱ ከተማ የሚገኝ መኖሪያ ቤት ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ተ/ር መኖሪያ ቤቱ የሚገኝበት አድራሻ የቦታዉ ስፋት በካ/ሜ. የባሌብትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር የቤቱ አገልግሎት የጨረታ መነሻ  ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ብር)
1 ቢሾፍቱ ከተማ ቀበሌ 02 200 BI/15729/10 ለመኖሪያ ቤት 2,871,127.00 287,112.00
 1. ተጫራቾች ለጨረታ የቀረበዉን መኖሪያ ቤት ፕሮግራም አሲይዘዉ በሥራ ሰዓት መጎብኘት ይችላሉ፡፡
 2. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በማንኛዉም የብርሃን ባንክ ቅርንጫፍ ክፍያ ፈፅመዉ ደረሰኙን በማቅረብ፣ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ከሚገኝበት ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት ከሚገኘዉ ወመሳድኮ ህንፃ 2ተኛ ፎቅ ፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ወይም ቢሾፍቱ ከተማ ስታድየም ፊት ለፊት ከሚገኘዉ ብርሃን ባንክ ቢሾፍቱ ቅርንጫፍ በመገኘት ለጨረታዉ የተዘጋጀዉን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡ ሆኖም ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸዉን ማቅረብ የሚኖርባቸዉ እና ጨረታዉ የሚከፈተዉ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት በሚገኝበት አዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘዉ ወመሳድኮ ህንፃ 2ተኛ ፎቅ ከፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ነዉ፡፡
 3. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ እና በዚህ የጨረታ ማስተወቂያ ላይ በተገለፀዉ መሰረት ለመኖሪያ ቤቱ የተጠቀሰዉን የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ በC.P.O. ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 4. ተጫራቾች መኖሪያ ቤቱን ሊገዙ የሚችሉበትን ዋጋ በተዘጋጀዉ የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም ላይ በመሙላት ከጨረታ ማስከበሪያ C.P.O ጋር አያይዘዉ በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ዘወትር በሥራ ሰዓት አስከ ሰኔ 07 ቀን 2014 ዓ/ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት በሚገኝበት አዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘዉ ወመሳድኮ ህንፃ 2ተኛ ፎቅ ከፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
 5. ጨረታዉ ሰኔ 07 ቀን 2014 ዓ/ም ቀን 2014 ዓ/ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በፋሲሊቲ መምሪያ ቢሮ ይከፈታል፡፡
 6. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ጨረታዉ በሚከፈትበት ቀንና ሰዓት ባይገኙ በሌሉበት ይከፈታል፡፡
 7. የመኖሪያ ቤቱ አሸናፊ ተጫራች፣ አሸናፊነቱ በተገለፀለት በ15 ቀናት ዉስጥ ያሸነፈበትን ዋጋ መክፈል ይኖርበታል፡፡
 8. በባንኩ የብድር መመሪያ መሰረት መስፈርቱን ለሚያሟሉ ተጫራቾች የብድር አቅርቦት ባንኩ ሊያመቻች ይችላል፡፡
 9. የጨረታው አሸናፊ በሚገዛዉ መኖሪያ ቤት ላይ የሚፈለግ ማንኛዉንም ለመንግስት የሚከፈሉ ግብር፣ ታክስ፣ የስም ማዛወሪያ ክፍያዎች እና የሊዝ ክፍያዎቹ መክፈል ይኖርበታል፡፡
 10. ባንኩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ለመሰረዝ ይችላል፡፡
 11. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0116182624 / 0116631729 ደዉለዉ ማግኘት ይችላሉ፡