የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ንብረት የሆነውንና በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ወለጋ ዞን ነቀምቴ ከተማ ወጋገን ሆቴል በመባል የሚታወቀውን ህንጻ ለትምህርት ቤት፣ ለህክምና ማዕከል ለቢሮ ለሆቴል ወዘተ ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል፡፡

Confederation-of-Ethiopian-Trade-Unions-CETU-Logo

Overview

 • Category : House & Building Rent
 • Posted Date : 05/21/2022
 • Phone Number : 0911928600
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 06/22/2022

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ንብረት የሆነውንና በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ወለጋ ዞን ነቀምቴ ከተማ በወረዳ 2 ቀበሌ 03 የሚገኘውንና በ3950 ካ.ሜ. ቦታ ላይ የተገነባውንና ቀደም ሲል ወጋገን ሆቴል በመባል የሚታወቀውን ህንጻ ለትምህርት ቤት፣ ለህክምና ማዕከል ለቢሮ ለሆቴል ወዘተ ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል፡፡

ህንጻው 4 ቢሮዎች፣ 1 የአንግዳ መቀበያ፣፣ 42 ክፍሎች፣ በቤት ውስጥ እና በመናፈሻ ግልጽ ስፍራ፣ የእንግዳ ማረፊያ እንዲሁም ለስብሰባና ለተለያዩ አገልግሎቶች መስጫ የሚውል ሁለገብ አዳራሽ፣ የከረንቡላ ማጫወቻ ክፍሎች፣  የልብስ ማጠቢያና የላውንደሪ አገልግሎት መስጫ ክፍሎች፣ በህንጻው ፎቅ አናት ላይ ለተለያዩ የመዝናኛ አገልግሎት መስጫ የሚውል 120 ካ.ሜ. ስፋት ያለው ሠገነት፣ መጋዘን፣ ሁለት የእንግዳ ማስተናገጃ ጎጆዎች የጥበቃ ቤት እና ከህንጻው ፊት ለፊትና በግቢው ውስጥ በቂ የተሽከርካሪ ማቆምያ አሉት፡፡

ስለሆነም በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መስፈርት መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

 • በተሰማሩበት የንግድ ሥራ ዘርፍ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፣
 • የዘመኑን ግብር የከፈሉና ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣
 • የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
 • ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ኢሠማኮ ፋይናንስ መምሪያ በግንባር በመቅረብ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
 • ተጫራቾች የሚከራዩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ከግንቦት 15 ቀን 2014 ዓ.ም. እስከ ግንቦት 26 ቀን 2014 ዓ.ም. እስከ ግንቦት 26 ቀን 2014 ዓ.ም. በሥራ ሰዓት ከታች በተገለጸው አድራሻ ማስገባት ይችላሉ፡፡
 • ጨረታው ግንቦት 29 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በኢሠማኮ ትንሹ ህንፃ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 311 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
 • ኮንፌዴሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- አዲስ አበባ ከመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ፍላሚንጎ አጠገብ በሚገኘው ኢሠማኮ ትንሹ ህንፃ 2ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 216 ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0911 92 86 00 ወይም 0912 66 33 80 መደወል ይችላል፡፡