የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ (አ.ማ) ያገለገሉ የተለያዩ ዓይነት 14 ተሸከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Cooperative-Bank-of-Oromia-S.C-Log-4

Overview

 • Category : Vehicle Sale
 • Posted Date : 05/21/2022
 • Phone Number : 0115576174
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 07/06/2022

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ (አ.ማ) ያገለገሉ የተለያዩ ዓይነት 14 ተሸከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

 1. የተሸከርካሪዎቹ ዓይነትና ዝርዝር ሁኔታ በጨረታው ሰነድ ላይ የሚገኝ ሲሆን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ እስከ ግንቦት 29 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ቅርንጫፍ ሂሳብ ቁጥር 1446500010001 ያገለገሉ የተለያዩ ዓይነት ተሸከርካሪዎች ጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 00 (ብር ሁለት መቶ) ገቢ በማድረግና ደረሰኙን በመያዝ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት ቦሌ ሩዋንዳ ራንግ ሪል ስቴት 7ኛ ፎቅ ከባንኩ ንብረት አስተዳደር ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
 2. የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች ብቻ የተሸከርካሪዎቹን ዓይነትና ዝርዘር ሁኔታ በአካል ማየት ለሚፈልጉ ብሄራዊ ቴአትር አካባቢ ከአዋሽ ባንክ ዋና መ/ቤት ጀርባ በሚገኘው የባንኩ ቅጥር ግቢ ውስጥ በመገኘት ግንቦት 19 ፣ 26 እና 29 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት መጎብኘት ይችላሉ፡፡
 3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ያገለገለ ተሸከርካሪ ዓይነቱንና የሠሌዳ ቁጥር በትክክል በመጥቀስ የሚገዙበትን ዋጋ ሰነድ ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ እስከ ጨረታ መዝጊያ ቀን ግንቦት 29 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት የባንኩ ንብረት አስተዳደር ቦሌ ሩዋንዳ ራንግ ሪል ስቴት 7ኛ ፎቅ በአካል ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውን በመላክ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 4. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ለእያንዳንዱ ያገለገለ ተሸከርካሪ የጨረታ መነሻ ዋጋውን 25% (ሃያ አምስት በመቶ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ ( CPO ) የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 5. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT ) 15% ጋር መሆን አለመሆኑን በግልጽ በሰነዱ ላይ ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡
 6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያልተያያዘለት የጨረታ ሰንድ ተቀባይነት የለውም ከውድድር ውጪም ይሆናል፡፡
 7. ጨረታው ግንቦት 29 ቀን 2014 ዓ.ም በ10፡30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ግንቦት 30 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ቦሌ ሩዋንዳ ራንግ ሪል ስቴት 7ኛ ፎቅ የስብሰባ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
 8. የጨረታው ዝርዝር ውጤት በባንኩ ሽያጭ ኮሚቴ እንደፀደቀ ለተጫራቾች ይገለፃል፡፡
 9. ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለተሸናፊ ተጫራቾች ወዲያውኑ የሚመለስ ሲሆን ለአሸናፊ ተጫራቾች ግን ላሸነፉበት ተሸከርካሪ ሙሉ ክፍያውን ከፍለው ንብረቱን ካነሱ በኋላ ተመላሽ ይሆንላቸዋል፡፡
 10. ማንኛውም ተጫራች ሌሎች ተጫራቾች በሰጡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
 11. አሸናፊ ተጫራቾች ላሸነፉበት ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች በፅሁፍ ከተገለጸበት ዕለት ጀምሮ በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ የሚፈለግባቸውን ክፍያ በመፈፀም ንብረቱን ማንሳት ይኖርባቸዋል ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ ውስጥ ክፍያውን ፈፅመው ንብረቶቹን የማያነሱ ከሆነ ባንኩ ጨረታውን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት 25% (CPO) ውርስ ይደረጋል ፡፡
 12. ለጨረታ የቀረቡት ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች ላይ የሚፈለግ ማንኛውም ዓይነት የስም ማዛወሪያ ለመንግሥት የሚከፈሉ የታክስ ክፍያዎችንና ሌሎች ወጪዎችን የጨረታ አሸናፊው ይከፍላል፡፡
 13. ባንኩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ (አ.ማ)

ስልክ ቁጥር 0115-576174

ፖ.ሣ.ቁ. 16936