መከላከያ ግንባታ ግብዓቶች ማምረቻ ድርጅት ከዚህ በታች የተገለፁትን የእንጨትና የኤሌክትሪክ ውጤቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Purchases
- Posted Date : 05/21/2022
- Phone Number : 0114352148
- Source : Reporter
- Closing Date : 07/02/2022
Description
መከላከያ ግንባታ ግብዓቶች ማምረቻ ድርጅት
DEFENCE CONSTRUCTION MATERIALS MANUFACTURING ENTERPRISE
የጨረታ ማስታወቂያ ግልጽ ጨረታ ቁጥር 17/2014
ድርጅታችን ከዚህ በታች የተገለፁትን የእንጨትና የኤሌክትሪክ ውጤቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት 1- የእንጨት ምርት ውጤቶች
ተ/ቁ | የእቃው ዓይነት | ሳይዝ | መለኪያ | ብዛት | የአንዱ ዋጋ | ጠቅላላ ዋጋ | አስተያየት |
1. | Panel MDF 3mm | 215X65 | በቁጥር | 630 | |||
2. | HDF Oak Clour/White Clour ወይም ስንዴ ከለር | 18mm | በቁጥር | 500 | |||
ድምር | |||||||
ቫት15% | |||||||
ጠቅላላ ድምር |
ሎት 2- የኤሌክትሪክ ምርት ውጤቶች
ተ/ቁ | የእቃው ዓይነት | ሳይዝ | መለኪያ | ብዛት | የአንዱ ዋጋ | ጠቅላላ ዋጋ | አስተያየት |
1. | Aluminum Wire Original | 1X70mm2 | በሜትር | 3000 | |||
ድምር | |||||||
ቫት 15% | |||||||
ጠቅላላ ድምር |
- ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያቸውን ሲያቀርቡ በዘርፋ የተሰማሩበትን የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣የተ.እ.ታ ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት፣ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት፤ የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)እእንዲሁም ወቅታዊ ግብር የከፈሉበትን ማረጋገጫ ፋይናንሺያል እና ኦሪጅናል ሰነድ ለይተዉ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በሚጫረቱበት የሎት አይነት አጠቃላይ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ በድርጅታችን ስም DCMME ባንክ ጋራንቲ ቦንድ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ለድርጅታችን ፋይናንስ የሥራ ሂደት ቡድን አስይዘው ደረሰኙን በጨረታ ወቅት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- አንድ ተጫራች በሚከፈተው ጨረታ መሠረት አነስተኛ ዋጋ ባቀረበው ድርጅት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም ከጨረታም ያሰርዛል፡፡
- የጨረታ አካሄዱ በመንግስት የግዢ መመሪያ መሠረት ይሆናል፡፡
- የሚሸጥ የጨረታ ሰነድ ስለማይኖር ተጫራቾች ከላይ በተዘረዘረው መሠረት ዋጋቸውን አቅርበው መጫረት ይችላሉ፡፡
- ተጨራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በዓሉት ተከታታይ ቀናት የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ሐሙስ ግንቦት 25/09/2014 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ቢሮ ቁጥር 17 ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሐሙስ ግንቦት 25 ቀን ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለው የተጫራቹ ፊርማ ከስርዙ ወይም ድልዙ ጎን መፈረምና በማህተም ማረጋገጥ አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የማጓጓዣውን ወጪ ችሎ ቃሊቲ ዋና መ/ቤት ግ/ቤት የሚያቀርብበት ዋጋ ማቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች አጠቃላይ ዕቃዎቹን አስገብተው ለማጠናቀቅ የሚያስፈልጋቸውን ግዜ መግለጽ አለባቸው
- ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ብቁ የሚሆነው በዝርዝር የተቀመጠውን የጨረታ መመሪያ ሲያሟላ እና በጨረታታመመሪያው መሠረት ሲያቀርብ ነው፡፡ የጨረታታመመሪያ ያላሟላ ተጫራች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከጨረታታ ውድድር ውጪ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ለድርጅታችን በቅጣት ገቢ የሚሆነው፣
- ጨረታው ተከፍቶ አሸናፊው ከመለየቱ በፊት ተጫራቹ ከጨረታው ወጥቻለው ካለ፤-
- የጨረታታአሸናፊው ጨረታታ ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች ሲያስረክብ በሚፈለገው መጠን አይነትና (Thickness) ወይም ጨረታውን ባሸነፈበት ናሙና መሠረት ሳይሆን ሲቀር፤-
- በማስረከቢያ ጊዜ በደረሰዉ የግዢ ትዕዛዝ መሠረት ሳይቀርቡ ወይም ሙሉ በመሉ ማስረከብ አለመቻሉ ሲረጋገጥ ነው፡፡
- ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማስታወሻ፡- ለተጨማሪ ማብራሪያ የስልክ ቁጥር 0114-35-21-48/49/50/ ወይም
0114- 34-87 43/45 መደወል ይቻላል፡፡