የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት የERP ሲስተም አማካሪ የአገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

Ethiopian-tourist-trading-enterprise-Logo

Overview

 • Category : Software purch. & Dev. Service
 • Posted Date : 05/21/2022
 • Phone Number : 0116610995
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 05/31/2022

Description

የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት

የ ERP ሲስተም አማካሪ የአገልግሎት ግዥ

ጨረታ ቁጥር 017/2014

ድርጅታችን የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት የERP ሲስተም አማካሪ የአገልግሎት ግዥ  በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

 1. በመስኩ በቂ ልምድና የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፣
 2. የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት ያላቸው፣
 3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ወረቀት ያላቸው፣
 4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን እስከ ግንቦት 23 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00-6፡30 እና ከሰዓት ከ7፡30 -11፡00 ሰዓት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00/አንድ መቶ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ።
 5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በአንድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በድርጅቱ ግዥ ንብረት አስተዳደርና ቴክኒክ ዳይሬክቶሬት ቢሮ 1ኛ ፎቅ እስከ ግንቦት 24 ቀን 2014 ዓ.ም በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን እስከ 4፡00 ሰዓት በመክተት ይታሸጋል። በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
 6. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፦ 22 ማዞሪያ ባቡር መሻገሪያ ቁጥር 1 ፊት ለፊት

 በስልክ ቁጥር፦ 0116-610995 /0116-622423 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት