የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር ከዚህ በታች በሎት የቀረቡትን የእሳት አደጋ ማጥፊያ ተሽከርካከሪዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Guraghe-Development-and-Cultural-Association-logo

Overview

  • Category : Vehicle Purchase
  • Posted Date : 05/21/2022
  • Phone Number : 0913415895
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 06/06/2022

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር ከዚህ በታች በሎት የቀረቡትን የእሳት አደጋ ማጥፊያ ተሽከርካከሪዎች አወዳድሮ  መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሠረት ጨረታውን መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተለውን ቅድመ ሁኔታዎች  ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

ሎት-1 የእሳት አደጋ ማጥፊያ ተሽከርካሪ 10,000 ሊትር ዉሃ እና 4,000 ሊትር ፎም መያዝ የሚችል

ሎት-2 የእሳት አደጋ ማጥፊያ ተሽከርካሪ 5,000 ሊትር ዉሃ እና 2,000 ሊትር ፎም መያዝ የሚችል

  1. ተጫራቾች በመስኩ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  2. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን ብር 10,000 ( አስር ሺ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከኦርጂናል ዶክመንት ጋር በማድረግ ማቅረብ የሚችሉ
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 ( አንድ መቶ ) በመክፈል ከማህበሩ ዋና ጽ/ቤት ቡታጅራና ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አ/አበባ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ  ቀናት መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ጨረታው በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  5. ፅ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የበለጠ መረጃ ለማግኘት በስልክ ቁጥር 046-115-03-12 ወይም 0913415895 ደውለው መጠየቅና መግዛት ይችላሉ፡፡

የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር