የነገው ሰው ትምህርት አክሲዮን ማኅበር የአክሲዮን ማኅበሩን የ2014 በጀት ዓመት ሂሣብ ሕጋዊ ፈቃድና ዕውቅና ባለው ኦዲተር ማስመርመር ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Auditing Related
 • Posted Date : 05/23/2022
 • Phone Number : 0116639043
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 06/03/2022

Description

የኦዲት አገልግሎት ጨረታ ማስታወቂያ

የነገው ሰው ትምህርት አክሲዮን ማኅበር የአክሲዮን ማኅበሩን የ2014 በጀት ዓመት ሂሣብ ሕጋዊ ፈቃድና ዕውቅና ባለው ኦዲተር ማስመርመር ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በዘርፉ የተሰማሩና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ በጨረታው መሣተፍ የሚችሉ መሆናቸውን እንገልፃለን፡፡

 1. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ከታች በተገለፀው አድራሻ በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
 2. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የአካውንቲንግ እና የኦዲት ቦርድ የሙያ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሠርተፊኬት፣ የዘመኑን የሥራ ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ የምሥክር ወረቀት ማስረጃ ከጨረታ ሠነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
 3. ጨረታው ግንቦት 26 ቀን 2014 ዓ.ም. በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአክሲዮን ማኅበሩ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡
 • ግንቦት 26 ቀን 2014 ዓ.ም. ከ8፡00 ሰዓት በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ማመልከቻ ተቀባይነት የለውም፡፡
 1. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድቦንድ 10% በባንክ በተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ (CPO)ማስያዝ አለባቸው፡፡
 2. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የነገው ሰው ትምህርት አ.ማ መገናኛ በተለምዶ ቀበሌ 24 ኮከብ ሕንፃ አካባቢ

     ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 5 መዝናኛ ክበብ ፊት ለፊት በሚገኘው ጽ/ቤት ( 011-663-90-43