ኦሮሚያ ባንክ የአክሲዮን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

Oromia-international-bank-logo-3

Overview

 • Category : Bank Related
 • Posted Date : 05/25/2022
 • Phone Number : 0115572080
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 06/08/2022

Description

   

 ኦሮሚያ ባንክ

         የአክሲዮን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ (LOT-15)

ኦሮሚያ ባንክ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በትውልድ ኢትዮጵያዊ ሆነው የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ባለአክሲዮኖች በባንክ ወይም በኢንሹራንስ ያላቸው የአክሲዮን ድርሻ እንዲመለስላቸው ባወጣው መመሪያ ቁጥር FIS/01/2016 መሠረት ሦስት ባለአክሲዮኖች ለቀው የወጡትን 7፣14፣27፣34 እና 111 አክሲዮኖች በጠቅላላው 193 አክሲዮኖችን ከዚህ በታች በተዘረዘረው አኳኋን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

 1. ተጫራቾች መግዛት የሚችሉት አነስተኛ የአክስዮን ብዛት 7፣14፣27፣34 እና 111 ሲሆን ከዚህ በታች የሆኑ አክሲዮኖችን ለመግዛት የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ እንዲሁም ለሽያጭ ለቀረቡት አክሲዮኖች የሚቀርበው ዋጋ ለእያንዳንዱ የአክሲዮን መጠን ለየብቻ ሊሆን ይገባዋል፡፡
 2. ተጫራቾች መጫረት የሚፈልጉትን የአክሲዮን ብዛት ጠቅላላ መነሻ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ቦንድ በባንክ ክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ አሰርተው እና ለዚህ ዓላማ የተዘጋጀውን ቅጽ ሞልተው አንድ ላይ በማያያዝ ከጨረታው ቀን በፊት አካውንቲንግና ትሬዥሪ መምሪያ 9ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 905 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 3. ጨረታው ሰኔ 01 ቀን 2014 ዓ.ም. 8:00 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸውና ታዛቢዎች በተገኙበት፣ ኦሎምፒያ አካባቢ በሚገኘው የኦሮሚያ ባንክ 10ኛ ፎቅ ዋናው መ/ቤት ውስጥ ይከፈታል፡፡
 4. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋጋ በአምስት (5) ቀናት ውስጥ ለባንኩ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
 5. ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው እና ለዚሁም በቂ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው፡፡ እንዲሁም ድርጅቶች ከሆኑ የድርጅቱ አክሲዮኖች በሙሉ ኢትዮጵያዊ በሆኑ ዜጎች የተያዙ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ በቂ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የማስረጃቸውን ፎቶ ኮፒ ከሚሞሉት ቅፅ ጋር አያይዘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 6. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-557-20-80/011-558-83-21 ዋናው መ/ቤት ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
 7. ተጫራቾች ሌሎች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
 8. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡