የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማኀበር ለዋናው መ/ቤት ፅ/ቤት፣ እና ለዋና መጋዘን/እስቶር/ አገልግሎቶች የሚውል ህንፃ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

Family-Guidance-Association-of-Ethiopia-logo-reportertenders-1

Overview

 • Category : House & Building Purchase
 • Posted Date : 05/25/2022
 • Phone Number : 0114672300
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 06/07/2022

Description

የህንፃ ግዢ ማስወቂ

BID No.: FGAE/HO/001/2022

የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማኀበር ላለፉት 56 ዓመታት በሥነ-ተዋልዶ ጤና ዘርፍ ለሀገሪቱ ኅብረተሰብ በተለይም ለእናቶች፣ወጣቶችና ሕፃናት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሲያበረክት የቆየ ሀገር በቀል መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው፡፡ ማኀበሩ ለህብረተሰቡ የሚሰጠውን አገልግሎት የበለጠ ለማጠናከር ለዋናው መ/ቤት ፅ/ቤት፣ እና ለዋና መጋዘን/እስቶር/ አገልግሎቶች የሚውል ህንፃ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መሥፈርቶች ባሟላ መልኩ ህንፃ ለመሸጥ የምትፈልጉ ህጋዊ የህንፃ ባለቤቶች ይህ ጨረታ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ ግንቦት 30 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ ሰነዱን ከማህበሩ ዋና መስሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 05 የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ከታች የተዘረዘሩትን ሰነዶች እና የዋጋ ማቅረብያ ሰነዳቸውን ለየብቻ በታሸጉ ፖስታዎች በዋናው መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 404 እስከ ማክሰኞ ግንቦት 30 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 6፡30 ስድስት  ሰዓት ተኩል ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በመክፈቻው እለት ለመገኘት በቻሉና በተገኙ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ፊት  ማክሰኞ ግንቦት 30 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 ሰአት ይከፈታል፡፡

ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተይዞ መቅረብ ያለባቸው ሰነዶች ዝርዝር በጨረታ ሰነዱ የተገለፁት ሆኖ የሚከተሉትን ያካትታል፡

 • የባለቤትነት ወይም የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ኮፒ
 • ሕንፃው ከማንኛውም የሶስተኛ ወገን የባለቤትነት ጥያቄ ነፃ መሆኑን ወይም እንዲሸጥ ስምምት መኖሩን የሚያሳይ ማስረጃ እና ከእዳና እገዳ ነፃ ማረጋገጫ ኮፒ
 • የፀደቀ ሳይት ፕላን፤ አርክቴክቸራል፤ እስትራክቸራል፤ ኤሌክትሪካል እና ሳኒተሪ ዲዛይኖች ኮፒ
 • የህንፃ ግንባታ ፍቃድ ኮፒ
 • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በተረጋገጠ የባንክ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም የባንክ ጋራንቲ ለጨረታ ያስገቡትን የመሸጫ ዋጋ 0.5% (ፐርሰንት) ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ለብቻው አሽገው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

የህንፃው መስፈርት በጨረታ ሰነዱ የተገለፁት ሆኖ የሚከተሉትን ማሟላት ይጠበቅበል፡

 • የምድር ቤቱን ሳይጨምር ቢያንስ ሶስት ፎቅ (G+3) እና ከዚያ በላይ የሆነ
 • ህንፃው ያረፈበት ጠቅላላ ወለል ስፋት የመኪና ማቆሚያን/ፓርኪንግ ጨምሮ ከ800ካሜ እስከ 1200ካሜ የሆነ
 • የግቢው ስፋት ቢያንስ 250 ካሬ ሜትርና ከዚያ በላይ የሆነ
 • ህንፃው የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማህበር ዋናው መ/ቤት አሁን አገልግሎት እየሰጠበት ከሚገኘው አካባቢ (ማለትም ሪቼ/መስከረም ማዞሪያ) አቅራቢያ በቦሌ እና በቂርቆስ ክፍለከተሞች የሚገኝ ህንፃ ቢሆን ይመረጣል

ማህበሩ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡

የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ በር ዋና /ቤት

ቂርቆስ /ከተማ ወረጤ 09 የቤት ቁጥር 1218

ደብረዘይት መንገድ፣ (ሪቼ አካባቢ)መስከረም ማዞሪያ ማዞሪያ በሚያስገባው መንገድ 400 ሜትር ገባ ብሎ

.. 5716፤ስልክ ቁጥር 251-114672300

አዲስ አበባ