የኢትዮጲያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የሞጆ ወደብና ተርሚናል ቅ/ፅ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : House and Office Furniture
- Posted Date : 05/29/2022
- Phone Number : 0221162181
- Source : Reporter
- Closing Date : 06/13/2022
Description
የጨረታ መለያ ቁጥር ሞ/ወ/ተ/008/2014
የኢትዮጲያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የሞጆ ወደብና ተርሚናል ቅ/ፅ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት ስምንት፡-የካፍቴሪያ ወንበር እና የመመገቢያ ጠረጴዛ
ሎት ዘጠኝ፡-የካፍቴሪያ የማብሰያ እና የመመገቢያ ዕቃዎች
በዚህም መሰረት፡-
- በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸዉ እና የዘመኑን ግብር ከፍለዉ ንግድ ፍቃዳቸዉን ያሳደሱና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣
- የአቅራቢነት ፍቃድ እዉቅና ያላቸዉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚህ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣
- ተጫራቾች የጨረታዉን ሰነድ የማይመለስ 100(አንድ መቶ)ብር በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ /15/አስራ አምስት የስራ ቀናት ዉስጥ ሞጆ ወ/ተ/ቅ/ፅ/ቤት በሚገኘው ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ 10,000(አስር ሺህ) ብር በንግድ ባንክ፣ህብረት ባንክ እና ኦሮሚያ ህ/ስ/ባንክ በተረጋገጠ CBO ከጨረታ ሰነዶች ጋር ማቅረብ ይናርበታል፣
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታዉን ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ በ 2(ሁለት) ፖስታ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15(አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ዉስጥ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- አንድ ተጫራች ባቀረበዉ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፣
- ማንኛዉም ተጫራች ለሚወዳደርባቸዉ ዕቃዎች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀዉ መሰረት ጨረታዉ ከመዘጋቱ በፊት ናሙና ማቅረብ ይኖርበታል፣
- ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ጨረታዉ በወጣ በ አስራ አምስተኛዉ(15)ቀን ላይ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኃላ የሚደርስ ማንኛዉም ሰነድ ሳይከፈት ለተጫራቹ ይመለሳል፡፡
- በተጫራቾች የሚሞላ ዋጋ ስርዝ ድልዝ የሌለዉ እና በግልፅ የሚታይ መሆን አለበት፡፡
- ቅ/ፅ/ቤቱ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ ፡-በስልክ ቁጥር 0221162181/0221162194 ደዉሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የኢትዮጲያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት
የሞጆ ወደብና ተርሚናል ቅ/ፅ/ቤት