ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዲሴቢሊቲ ኤንድ ዲቬሎፕመንት አሶሲዬሽን /ኢሲዲዲ/ በዋናው ቢሮ የሚገኝ የ2008 ሞዴል TOYOTA HIGH ROOF ተሽከርካሪ በሚገኝበት በድርጅታችን ቅጥር ግቢ ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Vehicle Sale
 • Posted Date : 05/29/2022
 • Phone Number : 0114165859
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 06/13/2022

Description

ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዲሴቢሊቲ ኤንድ ዲቬሎፕመንት አሶሲዬሽን /ኢሲዲዲ/ በዋናው ቢሮ የሚገኝ የ2008 ሞዴል TOYOTA HIGH ROOF ተሽከርካሪ በሚገኝበት በድርጅታችን ቅጥር ግቢ ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ድርጅትም ሆነ ግለሰብ በጨረታው ላይ መወዳደር ይችላል፡፡ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 2ዐዐ /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከድርጅቱ ቢሮ መውሰድ የሚቻል ሲሆን፡ የጨረታው ሰነድ ለመግዛት፡

 1. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ሰኞ እስከ ዓርብ ከጠዋቱ 3:00 – 11:00 ሰዓት) የጨረታ ሰነዱን በመግዛት ለጨረታ የሚቀርበው ተሽከርካሪ ድሪም ላይነር ሆቴል ጀርባ መስቀል ፍላወር አካባቢ በሚገኘው መስራቤታችን ዋና ቢሮ ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ ቀርበው መመልከት ይችላሉ፡፡
 2. ተጫራቾች ሊገዙት ለሚፈልጉት መኪና የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታው ሰነድ ውስጥ በተዘጋጅው ጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ አስገብተው ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ኢሲዲዲ ቢሮ በመምጣት ማስገባት ይችላሉ፡፡
 3. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት የመኪና ጨረታ ማስገቢያ /ቢድ ቦንድ/ የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 2ዐ በመቶ በድርጅቱ ስም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ ከጨረታ ዋጋ ማቅረቢያው ጋር በሰም በታሸገ ፖስታ ሲሰጡ አብሮ ከጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
 4. ጨረታው በ15ኛው ቀን ማለትም ሰኔ 05 ቀን 2014 ዓ/ም ተዘግቶ በቀጣዩ የስራ ቀን ማለትም ሰኔ 06 ቀን 2014 ዓ.ም ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚከፈት ሲሆን፣ አሸናፊው ወዲያው እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ የስያዘውን ሲፒኦ ታሳቢ በማድረግ ቀሪውን ገንዘብ በ5 ቀናት ውስጥ ከፍለው ተሽከርካሪውን የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡ በጨረታው አሸንፈው ከፍለው ለማይወስዱ ተጫራቾች ለጨረታው ማስረከቢያ /ቤድ ቦንድ/ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡ የጨረታ አሸናፊዎች መኪናውን የማጓጓዣ ወጪዎችን፤ ስም ማዞሪያና ሌሎች ማንኛውም ተያያዥ ወጪዎችን ይሸፍናሉ፡፡
 5. ጨረታው ለሚሸነፋት ያስያዙትን የጨረታ ዋስትና ማስረከቢያ/ቢድ ቦንድ/ የጨረታው አሸናፊ ሙሉ ክፍያውን አንደፈፀመ ተመላሽ የሚደረግላቸው ይሆናል፡፡
 6. ድርድቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ:- አዲስ አበባ ድሪም ላይን ሆቴል ቀጭን አስፖልት 35 ሜዳ መንገድ ገባ ብሎ   በሚገኘው ዋና ቢሮ

ለበለጠ መረጃ፡

በመስመር ስልክ ቁጥር ዐ114165859 ወይም ኢሜይል፡ Tenderecdd@ecdd-ethiopia.org ያግኙን።                                    

ኢሲዲዲ ዋናው ቢሮ