የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣንና ኃላፊነት መሰረት ከዚህ በታች በተመለከተው መሰረት ተስተካክለው እንዲሁም በተራ ቁጥር 4 እና 5 ላይ የተመለከቱ ተጨማሪ የመያዣ ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Commercial-Bank-of-Ethiopia-Logo-3

Overview

 • Category : House & Building Foreclosure
 • Posted Date : 05/30/2022
 • Phone Number : 0115574646
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 07/04/2022

Description

የሐራጅ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣንና ኃላፊነት መሰረት እሑድ ሚያዝያ 23 ቀን 2014 ዓ.ም በታተመው የሪፖርተር ጋዜጣ ላይ አውጥቷቸው ከነበሩት የሐራጅ ማስታወቂያዎች መካከል ከዚህ በታች በሰንጠረዡ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 3  የተመለከቱት ስህተት የነበራቸው በመሆኑ ከዚህ በታች በተመለከተው መሰረት ተስተካክለው እንዲሁም በተራ ቁጥር 4 እና 5 ላይ የተመለከቱ ተጨማሪ የመያዣ ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ የተበዳሪው ስም የንብረት አስያዥ ስም የመያዣ ንብረቱ መለያ የሐራጁ መነሻ ዋጋ (ብር) ሐራጁ የሚከናወንበት
አድራሻ የይዞታ መረጋገጫ ሰነድ ቁጥር የይዞታው ስፋት (በካ.ሜ) የይዞታው አይነት የሚሰጠው አገልግሎት ቀን ሰዓት
1 አቶ ሞና ተሾመ ገበየሁ ተበዳሪው ቡሌ ሆራ ከተማ ቀበሌ 01 BH/734/m.2032/2006 400 ለመጋዘን አገልግሎት የሚውል 1,016,645.63 23/10/2014 ዓ.ም 3፡00-4፡00 ጠዋት
በጉጂ ዞን፣ ሻኪሶ ከተማ ቀበሌ 01 WLEN/507/97 255.64 ለንግድ አገልግሎት የሚውል ቤት 826,423.18 23/10/2014 ዓ.ም 4፡00-5፡00 ጠዋት
2 ወ/ሮ ሃወኒ አሸናፊ ደያሳ ተበዳሪው አዳማ ከተማ አዱላላ ሃጤ ቀበሌ WLEN/4008 10,000 ለፋብሪካ አገልግሎት የሚውል ጅምር ህንፃ 33,951,259.41

 

23/10/2014 ዓ.ም 5፡00-6፡00 ጠዋት
3 ጉንዴ ሸባ የታጠበ ቡና ኃ/የተ/የግል ማህበር ጎንሳሞ ጉጋ አለታ ጬኮ 0531064 4.73 ሄክታር የቡና ማቀነበበሪያ ሳይት ከነማሽነሪው 5,659,419.81 23/10/2014 ዓ.ም 7፡0-8:00

ከሰዓት በኋላ

4 አቶ ተወልደ ግደይ ገ/እግዚያብሔር (አዲስ ኬብር) ተበዳሪው  

 

በፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ገላን ከተማ

B/M/G/K/L/I/178/2003 & B/M/G/K/L/I/83/20 20,000 የኤሌክትሪክ ኬብል ማምረቻ ፋብሪካ ህንፃ እና የተለያዩ ማሽነሪዎች 844,653,004.59 23/10/2014 ዓ.ም 8፡0-9:00

ከሰዓት በኋላ

B/M/G/K/L/54/2000 7,000 ለመጋዘን፣ ለእንግዳ ማረፊያ፣ ለቢሮ አገልግሎት የሚሰጡ 33,852,912.77 23/10/2014 ዓ.ም 9፡0-10:00

ከሰዓት በኋላ

5 ሄኖክ ወንድአፍራሽ ተበዳሪው በፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን፣ ኮሎቦ ከተማ 01 ጨፌ አደታ ሳይት ብሎክ 13 BMK/1341/2011 160  

ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውል በግንባታ ላይ የሚገኝ ይዞታ

640,815.48

 

 

 

 

24/10/2014 ዓ.ም 3፡00-4፡00 ጠዋት

ማሳሰቢያ

 1. ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪል የሐራጁን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) በማስያዝ መጫረት ይችላል፡፡
 2. የንግድ ማህበራትን ወክሎ ለመጫረት የማህበራቱን መመስረቻ እና መተዳደርያ ደንብ የያዘና በማህበራቱ ስም ንብረት ለመግዛት ስልጣን ያለው መሆን ያለበት ሲሆን ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ በማቅረብ ይሆናል፡፡
 3. የጨረታ አሸናፊ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ያለበት ሲሆን ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለሐራጁ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ተመላሽ አይደረግለትም፡፡
 4. ለመኖሪያ አገልግሎት በሚል ከተጠቀሱ ንብረቶች  ውጪ  ያሉ ንብረቶችን ተጫርቶ የገዛ ተጫራች በሽያጩ ገንዘብ ላይ 15 በመቶ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ታሶቦ ይከፍላል፡፡
 5. ንብረቱን ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ በመገኘት ወይም ባንካችን በሚያመቻቸው ፕሮግራም መሰረት መጎብኘት ይቻላል፡፡
 6. ጨረታው ከዚህ በላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዛጉዌ ህንጻ 8ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የባንኩ ሕግ ክፍል ውስጥ ይከናወናል፡፡
 7. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115-57-46-46 በመደወል ወይም ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አካባቢ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ዛጉዌ ህንጻ 8ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ህግ ክፍል በአካል ቀርቦ ማነጋገር ይቻላል፡፡