አልታድ ኢትዮጵያ ኃላ.የተ.የግ.ኩባንያ ታማኝና ብቁ የሆኑ የድርጅት የጥበቃ ሰራተኞች ስለሚፈልግ ከአቅራቢ ድርጅቶችን (ኤጀንቶች) አወዳድሮ አገልግሎቱን መግዛት ይፈልጋል፡፡

Altad-Ethiopia-Plc-Logo

Overview

 • Category : Textiles/ Fabrics & Wearing
 • Posted Date : 05/30/2022
 • Phone Number : 0115534852
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 06/06/2022

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ኩባንያችን አልታድ ኢትዮጵያ ኃላ.የተ.የግ.ኩባንያ ታማኝና ብቁ የሆኑ የድርጅት  የጥበቃ ሰራተኞች ስለሚፈልግ ከአቅራቢ ድርጅቶችን (ኤጀንቶች) አወዳድሮ አገልግሎቱን መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ተጫራቾች በሚያቀርቡት ጨረታ ሰነድ ጋር

 1. ለ2014 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ
 2. የምዝገባ ሰርትፊኬት
 3. የቫት ተመዝጋቢ ሰርትፊኬት
 4. ቲን ሰርትፊኬት
 5. በሙያው በቂ ልምድ ያላቸዉ
 6. ተጫራቾች ለስራው ያስገቡትን የጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡

የጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 7 የስራ ቀናት የማይመለስ 100 (አንድ መቶ) ብር በመክፈል መግዛት የሚችሉ መሆኑን እያሳወቅን ከላይ በዝርዝር በተገለፀው መሰረት ማሟላት የሚገባቸውን ሁሉ አሟልተው የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኢንቨሎኘ በማሸግ አልታድ ኢትዮጵያ ኃላ.የተ.የግ.ኩባንያ ዋናው መ/ቤት ካሳንችስ ከፍትህ ሚኒስቴር ወረድ ብሎ የቀድሞው ዮርዳኖስ ሆቴል ፊት ለፊት በሚገኘው የእናት ታወር 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 401 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ጨረታው ሰኞ በ29/09/2014ዓ.ም ከጧቱ 4፡00 ተዘግቶ 4፡30 ተጫራቾ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኩባንያው የስብሰባ አዳራሽ የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

አድራሻ፡

ለበለጠ መረጃ ፡- 011-553-48-52 / 011-553-09-27 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ