የድሬ ብድርና ቁጠባ ተቋም አ.ማ የተቋሙን የሠው ሀይል መመሪያ ከእነመዋቅራዊ አደረጃጀቱ ፣ የሥራ መዘርዝር ፣ የሠራተኞች ደመወዝ እና ጥቅማ ጥቅምን በአማካሪ ድርጅቶች (Consultants) አስጠንቶ ተግባራዊ ማድረግ ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Financial Consultancy
 • Posted Date : 05/30/2022
 • Phone Number : 0915754951
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 06/10/2022

Description

የጨረታ ማስታወቂያ            

የድሬ ብድርና ቁጠባ ተቋም አ.ማ የተቋሙን የሠው ሀይል መመሪያ ከእነመዋቅራዊ አደረጃጀቱ ፣ የሥራ መዘርዝር ፣ የሠራተኞች ደመወዝ እና ጥቅማ ጥቅምን በአማካሪ ድርጅቶች (Consultants) አስጠንቶ ተግባራዊ ማድረግ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የቀረቡትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም በመዋቅራዊ አደረጃጀት ፣ በደመወዝ እና ጥቅማ ጥቅም የጥናትና የማማከር ስራ ላይ የተሰማራ ድርጅት መወዳደር የሚችል መሆኑን ያስታውቃል፡፡

 1. የተቋም መዋቅራዊ አደረጃጀት የማማከር /የጥናት/ አገልግሎት ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፣
 2. በዚህ ዘርፍ የታደሰ የማማከር የንግድ ፈቃድ ያለው፣
 3. ቢያንስ በሶስት ብድርና ቁጠባ ተቋማት የተቋማቱን የስራ ስፋት እና የስራ ሁኔታ ገምግሞ የሠው ኃይል መመሪያ ፣ መዋቅር ፣ የሥራ መዘርዝር ፣ የደምወዝ እና ጥቅማጥቅም የማማከር /የጥናት/ ሥራ ልምድ ያለው፣
 4. የዘመኑን ግብር የከፈለ ፣
 5. የማማከር እና የሰነድ ዝግጅት ዋጋ ማቅረብ የሚችል፣
 6. ጥናቱን ለማጠናቀቅ የሚወስደው ጊዜ መገለጽ አለበት፣
 7. የተቋሙን መዋቅራዊ አደረጃጀት፣ ሠራተኞች የደመወዝ እና ጥቅማ ጥቅም ጥናትን ካጠናቀቀ በኋላ ለተቋሙ ማኔጀመንት እና ለስራ አመራር ቦርዱ በአካል ማቅረብ የሚችልና የሚሰጡ አስተያየቶችን በማካተት ሰነዱን አዳብሮ ማቅረብ የሚችል፣
 8. ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ለተከታታይ 10 ቀናት ቆይቶ በአስረኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ስዓት ላይ የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚያው ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት 10፡30 ድሬዳዋ በዋናው ቢሮ ይከፈታል፡፡
 9. ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ከተቋሙ የሚያስፈልጉ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የመስመር ስልክ ቁጥር 0251-124817 ወይም የተንቀሳቃሽ ስልክ 0915-754951 ወይም 0987-365325 ደውለው መጠየቅ የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

አድራሻ

ድሬዳዋ የፖስታ ሳጥን ቁጥር 2589

E-mail: teshomeabebe482@yahoo.com or

       /mulugetaa10@gmail .com/

የድሬ ብድርና ቁጠባ ተቋም አ.ማ

ድሬዳዋ