አራዳ አትክልት ተራ የገበያ ማዕከል አ.ማ በህንፃው ቤዝመንት ውስጥ የሚገኘውን ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለቀጣይ ሁለት ዓመት ማከራየት ይፈልጋል

Overview

  • Category : House & Building Rent
  • Posted Date : 05/30/2022
  • Phone Number : 0935401596
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 06/14/2022

Description

የፓርኪንግ (የመኪና ማቆሚያ) ቦታ ኪራይ ጨረታ

     አራዳ አትክልት ተራ የገበያ ማዕከል አ.ማ ፒያሳ በተለምዶ አትክልት ተራ ተብሎ በሚታወቀው 1588 ካ.ሜ ቦታ ላይ 3B+G+9 ህንፃ ገንብቶ ወደ ስራ የገባ መሆኑ ይታወቃል፤ በመሆኑም የአክሲዮን ማህበሩ ህጋዊ ይዞታ ክልል ውስጥ የሚገኘውን የመኪና ማቆሚያ ቦታ እንዲሁም በህንፃው ቤዝመንት ውስጥ የሚገኘውን ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለቀጣይ ሁለት ዓመት ማከራየት ይፈልጋል፤ በመሆኑም መጫረት የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ ቀጥሎ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኋል፡፡

  • የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤
  • ለ2014 ዓ.ም የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱና፤
  • የተ.እ.ታ ተመዝጋቢ የሆኑ፤
  • የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ /በጥሬ ገንዘብ 20,000.00 ብር በአክሲዮን ማህበሩ ስም የተዘጋጀ ማቅረብ የሚችል፡፡

በተጨማሪ ቦታውን በአካል በመመልከት የምትጫረቱበትን ወርሃዊ የኪራይ ዋጋ ተ.እ.ታ ጨምሮ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ከአክሲዮን ማህበሩ ጽ/ቤት የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመግዛት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ እስከ ሰኔ 6 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ እንድታስገቡ ያሳስባል፤ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማክሰኞ ሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ.ም ይከፈታል፡፡

አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ አዲስ አበባ ፒያሳ በተለምዶ አትክልት ተራ በሚገኘው የማህበሩ አዲስ ህንፃ

አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 01 የቤት ቁጥር አዲስ

4ተኛ ፎቅ የቤሮ ቁጥር ጂ4-024

ለተጨማሪ መረጃ በ0935 401596/95 መደወል ይችላሉ፡፡

አራዳ አትክልት ተራ የገበያ ማዕከል አ.ማ