አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውንና በሠንጠረዡ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Vehicle Foreclosure
- Posted Date : 06/04/2022
- Phone Number : 0115150711
- Source : Reporter
- Closing Date : 06/23/2022
Description
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውንና በሠንጠረዡ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋውን ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት/ንብረቶች መረከብ ይኖርበታል፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል፡፡
- ተበዳሪው/መያዣ ሰጪው በሐራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን ፣ ግብር ፣ በተጠቀሱት ንብረቶች ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ 15% እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጪዎችንም ገዢ ይከፍላል፡፡
- ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አሲዞ ለመጎብኘት ወይም ለማየት ይቻላል፡፡
- የጨረታው ቦታ በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 4 ላንቻ አካባቢ ህብረት ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ከነበረው ህንጻ ጎን ካለው አልፓውሎ ህንጻ 3ኛ ፎቅ በባንኩ ህግ መምሪያ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115-150711 እና 0115 54 67 37 አ.አ በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ስም | ከተበዳሪው የሚፈለግበት
ቀሪ ዕዳ |
የአሽከርካሪ ዓይነትና የተሰራበት ዘመን |
የሠሌዳ ቁጥር | የሻንሲ ቁጥር | የሞተር ቁጥር | የጨረታ መነሻ ዋጋ | ጨረታው የሚካሄድበት ቀን |
የምዝገባ ሰዓት |
የጨረታ
ሰዓት |
1
|
ክላውድ ወርልድ ዋይድ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር |
እስከ ጥቅምት 20 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ብር 43,372,160.13 |
አውቶሞቢል 2014 | አ.አ-01-35267 | MHFBW9F39F5017215 | 2NZ5447266 | 1,500,000.00 | ሰኔ 16 ቀን 2014 ዓ.ም | 4፡30-5፡30 | 5፡30-6፡00 |
አውቶሞቢል 2014 | አ.አ-01-36143 | MR2BW9F33F1065790 | 2NZ7186905 | 1,530,000.00 | ሰኔ 17 ቀን 2014 ዓ.ም | 4፡30-5፡30 | 5፡30-6፡00 |