የኢትዮጵያ መድኃኒት ፋብሪካ አክሲዮን ማህበር በድርጅቱ ቅጥር ግቢ በሚኘው መዝናኛ ክበብ የቁርስ፣የምሳ እና የእራት አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ብቃት እና አቅም ያላቸውን ድርድቶች የኮንትራት ስምምነት ውል አብሮ ለስራት ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Food Items Supply
 • Posted Date : 06/06/2022
 • Phone Number : 0939117633
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 06/14/2022

Description

የመዝናኛ ክበብ አገልግሎት ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ፣

 ድርጅታችን የኢትዮጵያ መድኃኒት ፋብሪካ አክሲዮን ማህበር በድርጅቱ ቅጥር ግቢ በሚኘው መዝናኛ ክበብ ውስጥ እና ቅርንጫፍ በቁጥር ከ5ዐዐ /አምስት መቶ/ በላይ ለሚሆኑ ሰራተኞቹ በሁለት ፈረቃ የቁርስ፣የምሳ እና የእራት አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ብቃት እና አቅም ያላቸውን ድርድቶች /ግለሰቦች/ በማወዳደር የተሻለ የምግብ አቅርቦት /አገልግሎት/ ምክንያታዊ በሆነ ዋጋ ማቅረብ ከሚችል ድርጅት /ግለሰብ/ ጋር ለተወሰነ ጊዜ በሚቆይ የኮንትራት ስምምነት ውል አብሮ ለስራት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ስለምግብ አገለግሎት አሰጣጣችሁ ያላችሁን የስራ ኘሮፖዛል ወይም ዝርዝር የስራ ዕቅድ አዲስ አበባ ከተማ፣ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 አስተዳደር ውስጥ ብስራተ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አለፍ ብሎ ካለው አደባባይ በሚኘው ዋናው ፋብሪካ ግቢ ጠቅላላ አገልግሎት ዋና ክፍል ቢሮ በመቅረብ በጨረታው ላይ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

በተጫራቾች የሚርበው ሰነድ /የስራ ዕቅድ/ ዉስጥ ሊያካትቱ የሚገባቸው ዝርዝር ነጥቦች፣

 1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው/ላት፤
 2. የተረጋገጠ የስራ ልምድ ወይንም የምስጋና ደብዳቤ ቢቻል ከሁለት ተቋማት /የማምረቻ ድርጅት ቢሆን ይመረጣል፣ ማቅረብ የሚችል፣
 3. የካፒታል መጠን የሚያሳይ ማስረጃ፣
 4. የሰራተኞችን አደረጃጀት በስራ ድርሻ፣
 5. የምግብ ዝርዝር ሜኖ /የቁርስ፣ የምሣ፣ የእራት እና ቡና፣ሻይ ተለይቶ ከነ ዋጋቸው፣
 6. ለምግብ ማዘጋጃ፣ ማስተናገጃ እና ለካባቢው ንፅህና የሚሰጠው ትኩረት፣

ማሳሰቢያ

 1. ተጨራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሰባት ተከታታይ የስራ ቀናት ዉስጥ እላይ በተጠቀሰው አድራሻ የተዘረዘሩ 6 ነጥቦችን ያካተተውን ሰነድ ከሰኞ እስከ ዐርብ ባሉት ቀናት ከጥዋቱ 2፡ዐዐ -11፡ዐዐ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
 2. የመዝናኛ ክበቡን ሁኔታ ዘወትር በስራ ሰዓት መመልከት ይችላሉ፡፡
 3. የሚቀርቡት ሰነዶች በስም በታሸገ ኢንቬሎኘ መሆን አለባቸው፡፡
 4. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከሰባት የሥራ ቀናት በኋላ ተዘግቶ በሚቀጥለው ቀን ጠዋት በ4፡ዐዐ ሰዓት ተጫራቾች በተገኙበት ይከፈታል፡፡
 5. ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 6. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0939117633 ወይም 0911 507635 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አድራሻ

የኢትዮጵያ መድኃኒት ፋብሪካ

በሣር ቤት መስመር ከብሥራተ

ገብርኤል ቤተክርስቲያን ወረድ ብሎ ካለው

የትራፊክ መብራት በስተቀኝ በኩል

ስልክ ዐ113 71 1ዐ ዐዐ/ዐ113 71 77 88