ሕብረት ባንክ አ.ማ ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልጽ ሐራጅ (ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡
Overview
- Category : House & Building Foreclosure
- Posted Date : 06/06/2022
- Phone Number : 0116625924
- Source : Reporter
- Closing Date : 07/07/2022
Description
የሐራጅ ማስታወቂያ፤
ሕብረት ባንክ አ.ማ. በቦሌ መድኃኒአለም፣ ምስራቅ እና ደብረ ብርሃን ቅርንጫፎች በኩል ለሰጠዉ ብድሮች በመያዣነት የያዛቸዉንና ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልጽ ሐራጅ (ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡
ተ.ቁ | የቅርንጫፍ ስም | የተበዳሪ ስም | የአስያዥ ስም | ቤቶቹ የሚገኙበት አድራሻና የቦታዉ ስፋት | የይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ቁጥር | የሐራጅ መነሻ ዋጋ በብር | ሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት | ጨረታው የወጣበት ጊዜ |
1 | ቦሌ መድኃኒአለም | ሱራፌል በቀለ ደግፌ | በቀለ ደግፌ ሞጆ | አዲስ አበባ ከተማ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 12፣የቦታ ስፋት 165 ካ/ሜ የሆነ ቦታ ላይ የሚገኝ የመኖሪያ ቤት | AA000081202489 | 5,645,552.00 | ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት | የመጀመሪያ |
2 | ምስራቅ | አፈወርቅ ተፈራ ወርቄ | አፈወርቅ ተፈራ ወርቄ | ደብረብርሀን ከተማ፣ቀበሌ 07፣የቦታ ስፋት 23,685 ካ.ሜ የሆነ ለት/ቤት አገልግሎት የሚውል ቤት | 1637 | 5,514,303.00 | ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ4፡00 እስከ 6፡00ሰዓት | የመጀመሪያ |
3 | ደብረብርሀን | ዘውዴ ፍቅሬ ኃ/ጊዮርጊስ | ጥሩነሽ ተሰማ ወ/ማርያም | ደብረብርሀን ከተማ፣ቀበሌ 02፣የቦታው ስፋት 512.70 ካ.ሜ የሆነ ለቅይጥ አገልግሎት የሚውል ህንጻ | 0952 | 3,474,742.00 | ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ ከ8፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት | የመጀመሪያ |
የሐራጅ ደንቦች
- ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊ የሆነዉ ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአስራ አምስት (15) ቀናት ዉስጥ አጠቃልሎ ካልከፈለ ያስያዘዉ ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሀራጅ ሲቀርብ ለሚታየዉ የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡
- በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪዎች እና አስያዦች ብቻ ናቸዉ፡፡
- በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሰው ንብረት የሐራጅ ሽያጩ የሚካሄደዉ በሕብረት ባንክ አ.ማ ዋናው መስሪያ ቤት ህብር ታወር ህግ አገልግለት መምሪያ 26ኛ ፎቅ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ነዉ፡፡ የሌሎች ንብረቶች ጨረታ ደግሞ ንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ ነው፡፡
- የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል፡፡ በሐራጁ ሰላሳ (30) ደቂቃዎች የተጫራች ምዝገባ አይካሄድም፡፡
- ለሐራጅ የቀረበዉን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልጉ ከአበዳረው ቅርንጫፍ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታዉ ቀን ሶስት ቀናት አስቀድሞ መጎብኘት ይችላሉ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸዉ በህግ የተወሰኑ የታክስና ግብር የስም ማዛወሪያ ጭምር /የጨረታዉ አሸናፊ/ ገዥዉ ይከፍላል፡፡
- ባንኩ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፣ ቦሌ መድኃኒአለም ቅርንጫፍ 011662 59 24/26/35፣ ደብረ ብርሃን ቅርንጫፍ 0116811141፣ ምስራቅ ቅርንጫፍ 0116621295፣ ወይም 0114-70-41-03/011-4-70-03-47 ሕግ አገልግሎት መምሪያ ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡