ሕብረት ባንክ ማየት ለተሳናቸው ግለሰቦች የኤ.ቲ.ኤም ስክሪን ላይ የድምፅ አገልግሎት ለመስጠት ይፈልጋል፡፡

hibret-bank-done-logo-reportertenders-4

Overview

 • Category : Bank Related
 • Posted Date : 06/06/2022
 • Phone Number : 0114706541
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 06/22/2022

Description

ጨረታ ቁጥር ሕባ/021/2014

የጨረታ ማስታወቂያ

ሕብረት ባንክ ማየት ለተሳናቸው ግለሰቦች የኤ.ቲ.ኤም ስክሪን ላይ የድምፅ  አገልግሎት ለመስጠት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ለኤ.ቲ.ኤም ስክሪን የሚውል የድምጽ ቀረፃ አገልግሎት ግዥ የሚሰጡ ድርጅቶች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት የጨረታ ሰነዱን ገዝተው መወዳደር ይችላሉ ፡፡

 1. ተጫራቾች ለዚህ ጨረታ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከሰኔ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በአካውንት ቁጥር IN0403007 አቅራቢያቸው በሚገኝ በማንኛውም የሕብረት ባንክ ቅርንጫፍ ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ ፡፡
 2. የጨረታ ሰነዱን የታደሰ ንግድ ፍቃድ በመያዝ የባንኩ ዋና መ/ቤት በሚገኝበት ልደታ ክ/ከተማ፣ ራስ አበበ አረጋይ መንገድ ሕብር ታወር 19ኛ ፎቅ ግዥ ዋና ክፍል በመገኘት መውሰድ ይቻላል፡፡
 3. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ሞልተው ከማስገባታቸው በፊት በጨረታ ሰነዱ ላይ የተካተተው የተጫራቾች መመሪያ በደንብ ማየት ይኖርባቸዋል፡፡
 4. በጨረታ ሰነዱ ላይ ያለውን የተጫራች መመሪያ ያልተከተለ ተጫራች ከውድድር ሊታገድ ይችላል፡፡
 5. እያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ መቅረብ አለበት፡፡
 6. እያንዳንዱ ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፀውን የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ወይም በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
 7. ተጫራቾች ሰኔ 15 ቀን 2014 ዓ.ም. እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በባንኩ ዋና መ/ቤት 19ኛ ፎቅ ግዥ ዋና ክፍል ማስገባት ይችላሉ፡፡
 8. ጨረታው ሰኔ 15 ቀን 2014 ዓ.ም. 8፡30 ባንኩ ዋና መስሪያ ቤት አራተኛ (4) ፎቅ ላይ በሚገኘው በባንኩ አዳራሽ ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
 9. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 10. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +25114 70 65 41 ወይም +251 11 467 3208 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

ሕብረት ባንክ