የኢትዮጵያ ሞተር እና ኢንጂነሪንግ ኩባንያ (ሞኤንኮ) የሥራ ልምድ ያላቸው አማካሪዎች አወዳድሮ የካፈቴሪያዎችን አደረጃጀት ፣ አወቃቀር ፣ የምግብና መጠጥ ቁጥጥር ስርአት ፣ የምግብ ማዘጋጃ ክፍል አደረጃጀትን ማስጠናት እና የተሻለ አደረጃጀት እና አወቃቀር እንዲኖራቸው ይፈልጋል፡፡

Moenco-logo

Overview

  • Category : Education & Training Services
  • Posted Date : 06/06/2022
  • Phone Number : 0911071500
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 06/21/2022

Description

የሠራተኞች ካፍቴሪያ አገልግሎት

አደረጃጀትን ለማማከር

ለሆቴል ባለሙያዎች የወጣ ጨረታ

የኢትዮጵያ ሞተር እና ኢንጂነሪንግ ኩባንያ (ሞኤንኮ) በአዲስ አበባ ዋና ቢሮ ፣ በአዳማ ቅርንጫፍ ፣ በሀዋሳ ቅርንጫፍ ፣ በድሬደዋ ቅርንጫፍ ፣ በባህርዳር ቅርንጫፍ እና በቃሊቲ ቅርንጫፍ መ/ቤቶች የሠራተኞች የምግብ አገልግሎት መስጫ ካፍቴሪያዎች አሉት ፡፡ እነዚህን የሠራተኞች ክበብ በዘመናዊ መልክ የበለጠ ለማደራጀት በሆቴል እና ሆስፒታሊቲ ሙያ የሥራ ልምድ ያላቸው አማካሪዎች አወዳድሮ የካፈቴሪያዎችን አደረጃጀት ፣ አወቃቀር ፣ የምግብና መጠጥ ቁጥጥር   ስርአት ፣ የምግብ ማዘጋጃ ክፍል አደረጃጀትን ማስጠናት እና የተሻለ አደረጃጀት እና አወቃቀር እንዲኖራቸው ይፈልጋል፡፡

በሙያው በቂ የሥራ ልምድ እና ተሞክሮ ያላቸው የሆቴል ወይም ሆስፒታሊቲ አማካሪዎች በሞኤንኮ ዋና መስሪያ ቤት የግዚ ክፍል በመምጣት የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00 – 10፡00 ሰዓት የጨረታ ሰነዱን በመውሰድ  መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን ፡፡

ማሳሰቢያ

  • ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ የማማከር ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡

አድራሻ ፣ ቦሌ መድሐኒያለም ሀያት ሆስፒታል ፊት ለፊት

0911071500/251-8090/የውስጥ መስመር 335