ናሽናል ሲሚንቶ አ/ማ ለድርጅቱ ጥበቃ ሠራተኞች ከዚህ በታች ለተገለጹት የአልባሳት አይነቶች በዘርፉ ላይ ከተሰማሩ አገልግሎት ሰጪዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Textiles/ Fabrics & Wearing
- Posted Date : 06/06/2022
- Phone Number : 0114401495
- Source : Reporter
- Closing Date : 06/22/2022
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ናሽናል ሲሚንቶ አ/ማ ለድርጅቱ ጥበቃ ሠራተኞች ከዚህ በታች ለተገለጹት የአልባሳት አይነቶች በዘርፉ ላይ ከተሰማሩ አገልግሎት ሰጪዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ቁጥር
- ዩኒፎርም ሙሉ ልብስ ሸሚዝና ሱሪ (ሸሚዙ እጅጌ ሙሉ) ካኪ (ኮተን) ቀለም 270
- የሸሚዙ የግራ ደረት ኪሱ ላይ የድርጅቱ አርማ በጥልፍ መልክ (Embroidery type) ያለው 270
- ኮፍያ የጥበቃ ካኪ (ኮተን) ቀለም 270
- ቀበቶ (Belt for trouser for secuirty) 270
- ጫማ (Shoes for security 270
በመሆኑም ተጫራቾች
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ከላይ የተገለጸውን አልባሳት አይነቶች የአንዱን ዋጋ በግልጽ በማስቀመጥ እንዲሁም የአልባሳቶቹን ስፌት ናሙና (sample) ሳር ቤት ግደይ ገ/ህይወት ህንጻ 3ኛ ፎቅ አ.አ. ስልክ፡ 251-114-401495 /0921-16-04-44 ግዢ ክፍል እና ድሬዳዋ ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ ስልክ ቁጥር 0935-98-50-83/0946-43-93-94 ግዢ ክፍል በታሸገ ፖስታ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ላሉት 3 ወራት ህጋዊ ሆኖ የሚቆይ የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ. 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ) ብር ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ቀናት የሚቆይ ሆኖ ማለትም ሰኔ 14/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ጨረታው ተዘግቶ ሰኔ 17/2014 ዓ.ም ድሬዳዋ በሚገኘው ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
ማሳሰቢያ፡-
ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ተከፍቶ ውሳኔ ይሰጥበታል፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
ድርጅቱ!