አልፋ ኢንተርናሽናል ኃ.የተ.የግ.ማህበር ከአገልግሎት ዉጭ የሆኑ ሶስት መጅሩስ መኪኖችንና ተሸከርካሪዎችን ግምታቸዉ 54 ኩንታል ወይም (54‚000ኪ.ግ) ባሉበት ሁኔታ ቆራርጦ ለመዉሰድ ለሚፈልጉ ተጫራቾች አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Overview

  • Category : Other Sale
  • Posted Date : 06/08/2022
  • Phone Number : 0116475749
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 06/16/2022

Description

የጨረታ  ማስታወቂያ

አልፋ ኢንተርናሽናል .የተ.የግ.ማህበር  ከአገልግሎት  ዉጭ የሆኑ ሶስት  መጅሩስ መኪኖችንና ተሸከርካሪዎችን  ግምታቸዉ 54 ኩንታል ወይም (54‚000ኪ.ግ) ባሉበት ሁኔታ  ቆራርጦ ለመዉሰድ  ለሚፈልጉ ተጫራቾች አወዳድሮ  ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡በዚሁ መሠረት በጨረታዉ መካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-

  1. ተሸከርካሪዎች ባሉበት ቦታ አያት አክሲዮን ዞን 3 ቅጥር ግቢ 2ቱ  ሲገኙ  አንዱ    መኪና ቦሌ ለሚ  በሎ  ከሚባለዉ  ከድርጅቱ  ሳይት ግቢ ማየት ይቻላል፡፡

2.ተጫራቾች  ለመወዳደር  የአንድ ኪሎ የመግዣ  ዋጋን   ቫትን ጨምሮ ዋጋቸዉን ማቅረብ ይቻላሉ፡፡

  1. ማንኛዉም ተጫራች ለመጫረት ተመላሽ የሚሆን 100‚000(መቶ ሺህ ብር ) ማስያዣ በሲፒኦ(CPO) ከዋጋዉ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ለአሸናፊዉ ድርጅት (ግለሰብ) ከሂሳቡ ላይ በመጨረሻ  ተቀናሽ ይሆንለታል፡፡ጨረታዉን  ያላለፉ ተመላሽ  ይሆናል፡፡አሸናፊዉ ድርጅት (ግለሰብ) ካሸነፈ በኋላ  ግደታዉን   የማይወጣ ከሆነ ማስያዣዉ ገንዘብ  አይመለስም፡፡
  2. አሸናፊዉ ድርጅት (ግለሰብ) ከላይ በተጠቀሰዉ ግምታዊ ኪ.ግ. የአሸነፈበትን ዋጋ 25% ለድርጅቱ ገቢ  ያደርጋል፡፡
  3. የጨረታዉ አሸናፊ ቁርጥራጩን ብረት ከመጫኑ በፊት የሚጭንበትን  መኪና በባዶዉ  ከሻጭ ድርጅት ወኪል ጋር በመሆን  የሚጭንበትን መኪና  ያስመዝናል ፣ ጭኖ ከጨረሰም  በኋላ  ያስመዝናል፡፡ ስለዚህ  የመጫንም  ሆነ  የማስጫን  ስራዉ የጨረታዉ አሸናፊ   ነዉ፡፡
  4. የጨረታዉ አሸናፊ ካስመዘነ በኋላ ወዳያዉኑ በአሸነፈበት የኪሎ ግራም   ሂሳብ ታስቦ ሂሳቡን  ይከፍላል፡፡ 24 ሰዓት ካለፈ   10% ያስቀጣል፡፡

7.ይህ ማስታወቂያ   በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ  ጀምሮ 7 ተከታታይ   ቀናት  ዉስጥ ጃክሮስ  አካባቢ  በሚገኘዉ ቢሮ  ማቅረብ ይቻላል፡፡

ማሳሰቢያ፡-ጨረታዉን የጨረታ ኮሚቴዉ አሸናፊዉን ድርጅት(ግለሰብ) ያሳዉቃል፡፡ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ  ካገኜ  በጨረታዉ  አይገደድም፡፡

ለተጨማሪ መረጃ  ..  -0116475749 -0913293636/0973136030