ዳሽን ቢራ ፋብሪካ አ.ማ. ወላይታ ሶዶ እና አሶሶ መስመር የዳሽን ቢራ ምርቶችን ለማከፋፈል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡

Dashen-Brewery-logo

Overview

  • Category : Alcohol & Soft Drinks
  • Posted Date : 06/08/2022
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 06/28/2022

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ዳሽን ቢራ ፋብሪካ አ.ማ. ወላይታ ሶዶ እና አሶሶ መስመር የዳሽን ቢራ ምርቶችን ለማከፋፈል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው
  2. በቂ ተሽከርካሪ ማቅረብ የሚችል (የራሱ ቢሆን ይመረጣል)
  3. ምርቱን ለማከማቸት የሚሆን መጋዘን (የራሱ ሲሆን ይመረጣል)
  4. በዘርፉ ተዛማጅ የሥራ ልምድ ያለው
  5. የሥራ ማስኬጃ በቂ ካፒታል ያለው መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ በአካባቢው ለረጅም ጊዜ ነዋሪ የሆነና በአካባቢው ማህበረሰብ መልካም ስም ያላቸው፤
  6. ማህበራዊ እና ህጋዊ ግዴታዎችን በአግባቡ እየተወጣ ያለና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤

ተጫራቾች ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15(አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን ሠነድ አሟልተው አዲስ አበባ፤ ዳሽን ቢራ ፋብሪካ ዋና መስሪያ ቤት (22 የቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት አጠገብ) ከሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ ለዚህ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በብር 300 (ሦስት መቶ ብር) ገዝቶ በመሙላት ጨረታውን መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን ጨረታው ሰኔ 01/2014 ዓ.ም. ድረስ አየር ላይ የሚቆይ መሆኑን እየገለጽን፡፡ ጨረታው ሰኔ 21 ቀን 2014 ዓ.ም. ከሰዓት 8፡30 ተከፍቶ ቀጣይ ባሉት ተከታታይ 5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ውጤቱን የምናሳውቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡