ሰላም የህዝብ ማመላለሻ አ.ማ የኩባንያው ወርክ ሾፕ ግቢ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ያገለገሉ ቁሳቁሶች (scrap materials) አወዳድሮ በጨረታ ለመሸጥና አዳዲስ መለዋወጫዎች ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Purchases
 • Posted Date : 06/10/2022
 • Phone Number : 0914706518
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 06/21/2022

Description

ድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ሰላም የህዝብ ማመላለሻ አ.ማ የኩባንያው ወርክ ሾፕ ግቢ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ያገለገሉ ቁሳቁሶች (scrap materials) አወዳድሮ በጨረታ ለመሸጥና አዳዲስ መለዋወጫዎች ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ግዢ  LOT-1

1ኛ. ቱዩብለስ ጎማ ለመግዛት (295/80R-22.5) የሆነ ዋስትና ሊሰጥ የሚችል፡፡

2ኛ. ብሬክ ፓድ

3ኛ. ለሰራተኞች ዩኒፎርም ሸሚዝ፤ኖርማል ጫማ፤ሴፍቲ ጫማ፤ቱታ፤ጋዎን ለመግዛት፡፡

4ኛ. የሞተር ዘይት(15w/40)የራዲያተር ኩላንት እና የመሳሰሉት፡፡

የሚሸጥ LOT-2

5ኛ. የተለያዩ የአውቶብሱ የቦዲ አካላ እና ያገለገሉ ብሬክ ፓዶች ጎማዎች ፊልትሮዎች ባትሪዎች ፍሪሴን ሸራዎች የተቃጠለ ዘይት ከነበርሜሉ እንዲሁም ቁርጭራጭ ብረቶች በኪሎ ለመሸጥ ስለሚፈልግ ፍላጎቱ ያላቸው ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

ስለዚህ ፡-

 1. በየዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው አቅራቢዎች የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የምዝገባ ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት እና TIN ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
 2. ለዚህ ጨረታ ተብሎ የተዘጋጀውን ጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 07 (ሰባት) የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ)በመክፈል  ዮሴፍ ቤተ ክርስትያን አጠገብ ጋራጅ ባለው ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
 3. ለጨረታ ማስከበርያ ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ የሚችል፡፡
 4. ለተራ ቁጥር አንድ እና ሁለት 150,000 (አንድ አቶ ሃምሳ ሺ) ለተራ ቁጥር ሶስት ለዩኒፎርምና ጫማ ግዢ 30,000 (ሰላሳ ሺ) ለተራ ቁጥር አራት ዘይትና ራዲያተር ኩላንት እቃዎች ግዢ 30,000(ሰላሳ ሺ) ለተራ ቁጥር አምስት ያገለገሉ እቃዎች 15,000(ሰአስራ አምስት ሺ) ማስያዝ የሚችል፡፡
 5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኢንቨሎፕ ዬሴፍ ጋራጅ በሚገኘው ቢሮ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ጨረታዉ በሰባተኛው ቀን ከሰዓት በ9፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በ9፡30 በድርጅቱ መሰብሰብያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
 6. አሸናፊ ድርጅት ወይም ድርጅቶች አሸናፊነታቸው በተገለፀ በአስር ቀናት ዉስጥ ዕቃውን ማስገባት ወይም ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡
 7. ተጫራቶች ለምንገዛው ቱዩብለስ ጎማና ለዩኒፎርም፣ ሸሚዝ፣ ኖርማል ጫማ፣ ሴፍቲ ጫማ፣ ቱታ፣ ጋዎን ብሬክ ፓድ የሞተር ዘይት ራዲያተር ኩላንት እና የመሳሰሉትን የያንዳንዱ ዋጋ ከነቫቱ በመሙላት ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 • ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነዉ፡፡

ሰላም የሕዝብ ማመላለሻ አክስዮን ማህበር

ዮሴፍ ቤተክርስትያን ፊት ለፊት

አዲስ አበባ 

ለተጨማሪ ማብራሪያ   በስልክ ቁጥር 0914706518/0912994892 ደውለዉ ይጠይቁ