ካዲላ ፋርማሲውቲካልስ ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግል ማህበር መድሀኒት ወደተለያዩ አካባቢዎች ለማጓጓዝ የሚሆን አይሱዙ ወይም ኤፌሳአር አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን ወይም ግለሰቦችን አወዳድሮ ለአንድ አመት ኮንትራት በመፈራረም ማሰራት ይፈልጋል፡፡

Cadila-pharmacesticals-logo

Overview

 • Category : Transport Service
 • Posted Date : 06/10/2022
 • Phone Number : 0114450257
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 06/24/2022

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን ካዲላ ፋርማሲውቲካልስ ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግል ማህበር በፊንፊኔ ልዩ ዞን ገላን ከተማ ከሚገኘው የመድኃኒት ፋብሪካ ቀጥሎ ባለው ዝርዝር መሠረት ከድርጅቱ የሚወጣ ፍሳሽ ቆሻሻ ለማስነሳት የፍሳሽ ማስወገጃ ቦቲ መኪና  እና የድርጅቱ ምርት የሆነውን መድሀኒት ወደተለያዩ አካባቢዎች ለማጓጓዝ የሚሆን አይሱዙ ወይም ኤፌሳአር አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን ወይም ግለሰቦችን አወዳድሮ ለአንድ አመት ኮንትራት በመፈራረም ማሰራት ይፈልጋል፡፡

 1. በዚሁ መሰረት በ ISUZU የጭነት አገልግሎት የሚሰጥ  
ለአዲስ አበባና አካባቢው  
ተ/ቁ መነሻ ማድረሻ  

ለአንድ ጉዞ የተቀመጠ ዋጋ

1 ገላን አቃቂ/ቃሊቲ እና አካባቢው  
2 ገላን ዱከም፣ ደ/ዘይት እና አካባቢው  
3 ገላን ሳሪስ፣ ሃናማርያም፣ አዲሱሰፈር፣ ጐተራ፣  
4 ገላን አየርጤና፣ ልደታ፣ ጦርኃይሎች፣ መካኒሳ፣ ካዛንችስ፣ ቦሌ፣ ገርጅ፣ መርካቶ እና አካባቢው  
5 ገላን ፒያሳ፣ ኮተቤ፣አዲሱገበያ፣ ሸጐሌ፣ መገናኛ፣ ሲኤምሲ፣ ፓስተር፣ታጠቅ፣ እንጦጦ እና አካባቢው  

የፍሳሽ ቆሻሻ ማንሻ ቦቲ

 • 15,000 ሊትር እና ከዚያ በላይ የመጫን አቅም ያለው ተሽከርካሪ ባለቤት የሆነ
 • ይህንኑ አቅም የሚያረጋግጥ የብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ ከሚመለከተው ክፍል ማቅረብ የሚችል፡፡
 • በቀን ሁለት ጊዜ የፍሳሽ ቆሻሻውን የድርጅቱ ፋብሪካ ከሚገኝበት ገላን ከተማ ማንሳት የሚችል
 • ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሠርተፍኬት ያለው፡፡
 • የኢንሹራንስ ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችል

ማንኛውም ተወዳዳሪ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አንድ ጊዜ ለሚያነሳው ፍሳሽ ቆሻሻ የሚጠይቀው የአገልግሎት ክፍያ መጠን አና ለጭነት ማጓጓዣው የአንድ የጉዞ ታሪፍ በመጥቀስ እና  ከላይ የተገለፁትን ማስረጃዎች እና ሊብሬ ኮፒ በታሸገ ፖስታ ውስጥ በማድረግ ማመልከት የሚችል መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የማመልከቻ መቀበያ ቦታ አዲስ አበባ መስቀል ፍላወር ከድሪም ላይነር ሆቴል ፊት ለፊት ጥበቡ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ወይም ገላን ከተማ ከኖክ ነዳጅ ማደያ ከፍ ብሎ በሚገኘው የድርጅቱ መድሀኒት ፋብሪካ ውስጥ አስተዳደር ቢሮ ነው፡፡

ድርጅቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-4-45-02-57/58 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡