ተፈዘር የገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበር የ2013 እና 2014 ዓ.ም የማህበሩን ሂሳብ ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Auditing Related
 • Posted Date : 06/12/2022
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 06/21/2022

Description

       የኦዲት ጨረታ ማስታወቂያ

ተፈዘር የገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበር የ2013 እና 2014 ዓ.ም የማህበሩን ሂሳብ ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡

 1. የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ወይም እሱ ከሚወክለው አካል ሂሳብ ለመመርመር የሚያስችለውን የሙያ ፈቃድ ያገኘና የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፤
 2. በሀገሪቱ ህግ መሰረት የኦዲት ሥራ ለመስራት የሚያስችል ወቅታዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው፤
 3. የህብረት ሥራ ማህበራት ሂሳብ ምርመራን በተመለከተ የፌዴራል ህብረት ሥራ ኤጀንሲ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ህብረት ሥራ ኤጀንሲ ወይ ከሌሎች ህጋዊ አካላት ሥልጠና የወሰደ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ቢሆን ይመረጣል፤
 4. ተወካዩ የሂሳብ መርማሪ ወይም ከሂሳብ መርማሪው ቡድኑ አባላት ውስጥ ቢያንስ አንዱ ከዚህ በፊት የህብረት ሥራ ማህበራትን ሂሳብ የመረመረ ቢሆን ቅድሚያ ይሰጠዋል፤
 5. የህብረት ሥራ ማህበሩን ሂሳብ ለመመርመር ብዙ ባለሙያዎችን በሥራ ላይ ማሰማራት የሚችል ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሚከተለው ማንኛውም ኪሳራና ችግር አስቀድሞ ኃላፊነቱን የሚወስድ፤
 6. እንደአስፈላጊነቱ አግባብ ባለው ባለስልጣን የሚጠየቁ ሌሎች መረጃዎችን ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት
 7. የሚወዳደሩበት ዋጋ በስም በታሸገ ኢንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 7 የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 እና ከሰዓት ከ7፡30 እስከ 11፡00 ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
 8. የጨረታው ምዝገባው በተጠናቀቀ በቀጣይ የሥራ ቀን ከሰዓት 10፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ እለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በራሳቸው ምክንያት መገኘት ካልቻሉ ጨረታው በተገኘው ሰው ይከፈታል፡፡